Gudumaale

   Sidaamu Daga Budu Battala
Connecting Sidama People

ከልል የመሆን ጥያቄ በፌዴራል ሥርዓት፣ የሲዳማ ጥያቄ ከኣጭር ሌሎች ሀገሮች ተሞከሮ ኣንፃር

በዚህ ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱን በመግለጽ ወንድሞቻችን ደስታችውን በመግለጽ ላይ መሆናችዉን ለማየት ይቻላል። በቅርቡ መደበኛ ስብሰባዉን ያካሄደው ኢህኣድግን ጨምሮ በያዝነው ሰሞን ከተገማገመው ደኢህደን ድረስ የሲዳማን ሀዝብ ክልል የመሆን ጥያቄ ከመመለስ ውጪ ሌላ አማራጭ ሊኖር እንደማይችል ለማመን የተገደዱ ይመስላል።

በዚህ ኣጭር ጽሁፍ በሌሎች የፈደራል ስርኣት በሚከተሉ ሀገሮች ክልል መጠየቅ ምን ገጽታ እንዳለዉ በኣጭሩ ለማሳየት ተሞክሮኣል። በ1987 በጸደቀው ህገመንግስት መሰረት ኢትዮጵያ ፈደራላዊና ደሞክራሲያዊት ሀገር ናት። በፈደራል ስር የሚተዳደሩ ሀገሮች በክልሎች የተዋቀሩ እንደመሆናቸዉ የፈደራል መንግስትና የክልል መንግሰታት የሚባሉ አካላት በህገመንግስቱ ተቆጥሮ የተሰጣችውን የየራሳችዉ የስልጣን ድርሻ ያስተዳድራሉ።

በዚህም ኣስተሳሰብ ፌዴራልዝም ማለት፣
Federalism is a philosophy, doctrine and arguably an ideology (Watts, 1988) that favors a distinct territorial pattern of government, one that combines the centralization of the some political powers and the decentralization of others. Federalism. A principle of government that defines the relationship between the central government at the national level and its constituent units at the regional, state, or local levels.

በዚህም መሠረት ፌዴራልዝም የኣስተዳደር ፍልስፍና ሲሆን ፌዴሬሽን የሚለው ቃል ግን የመንግስታትን መዋቅር ወይም ኣደረጃጀትን የሚመለከት ፅንሰ ሃሳብ ነው። በኣለማችን ላይ 38% የሚሆነዉ ህዝብ በዚህ ሰርኣት ይተዳደራል። ለምሳ፣ ኣሜሪካ፣ ካናዳ፣ ህንድ፣ ስዊዘርላንድ፣ ናይጀሪያ፣ በልጂየም፣ ደቡበ ኣፍሪካ፣ ኢትዮጵያ፣ ጀርመን፣ በራዚል፣ መክስኮ፣ ኣውስትሪያ፣ ኣውስትራሊያ፣ ራሽያ፣ ኢራቅ ወዘተ።

እንዳነሳነው በመርህ ደረጃ ፌዴሬሽኖች በክልሎች የተዋቀሩ ሲሆን የክልሎቹ ቁጥር ህገመንግስቱ ሲፀድቅ ከነበረበት ሊጨምር የሚችልበት እድል ሊኖር ይችላል። እሳቤውም የፖለቲካ ሳይንስ ልህቃን እንደሚሉት ( States are not static, unchanging and permanent, rather states would evolve and change ). ባጭሩ መንግስታት በጊዜ ሂደትና በሌሎች ተለዋዋጭ ኩነቶች ምክንያት ቋሚ ኣይደሉም፤ )

በዚህም የመንግስታቱ የውስጣዊና ውጫዊ የፖለቲካ ሂደት ሲቀየር በፌዴሬሽኖችም ውስጥ ነባር ክልሎች ቁጥር ጨምሮ ከፍ ሊል ወይም በሚፈጠረው ውህደት ምክንያት ቁጥሩ ሊቀንስ ይችላል።
===========================================================
የሲዳማ ህዝብ ክልል ይገባኛል ጥያቄን በርካቶች ሲያብጠለጥሉና ብስጋት ሲያዩ ይስተዋላል። የተወሰነው ቡድን ከብሔርተኝነት ጋር በማያያዝ፣ የኢትዮጵያን ኣንድነት የሚፈታተን ኣድርጎ ሲያቀርብ፣ ሌሎች ወገኖች ደግሞ የሲዳማ ክልል ምስረታዉ የፌዴራል ሥርዓቱ እንዳይረጋጋ ያደርጋል፣ ደቡብ የተባለውን እሥር ቤት እንዲፈርስ ያደርጋል፤ የሚል ምክንያት ያቀርባሉ። በኣብዛኛዉ ሀሳቡን የሚሠነዝሩ ወገኖች ሲዳማ የመብት ጥያቄን የመብት ሳይሆን ከኢትዮጵያ የመገንጠል ያህል ኣድርገዉ ኣጠልሽተዉ ያዩታል። ያቀርቡታልም።
የሌሎች ፌዴራል ሥርዓት የሚከተሉ ሀገሮች ኣጭር ተሞክሮ
======================================================================
ቀጥለን የሌሎች ፌዴራል ሥርዓት በሚከተሉ ሀገሮች ክልል የመሆን ሁኔታን እናያለን።
1. የህንድ ፌዴሬሽን፤ 
ህንድ ፌዴራል ስርዓት ከሚከተሉ ሀገሮች መካከል ዋነኛ ናት። ሕንድ በኣሁኑ ጊዜ 29 ክልሎች፣ 7 የህብረቱ ቀጠናን ጨምሮ በጠቅላላዉ 36 ክልሎች ይገኙባታል። ህንድ ከብሪታኒያ ኣገዛዝ ነፃ ወጥታ ህገመንግስት ስታቋቁም ፫፺ ሚሊዮን ህዝብ የነበራት ሲሆን 12 የክልል መንግስታት ነበሩኣት። እ ኣ ኣ 1957 የፀደቀው ህገመንግስት በኣንቀጽ 3ሀ ላይ ተጨማሪ ክልሎችን ማደራጀት እንደሚቻል በደነገገው መሠረት በርካታ ክልሎች ተደራጅተዋል። suvir Rashuvansh (2016) የሚባሉ የህንድ ምሁር በዚህ ዙሪያ ባካሄዱት ጥናት የቋንቋ ብዝሃነትና ክልላዊ ፍላጎቶች ለክልሎቹ ቁጥር መጨመር ምክንያት መሆናቸዉን ይጠቅሳሉ። በኣሁኑ ጊዜ ህንድ በ29 ክልሎችና 7 የዩኒየን ግዛቶች ባጠቃላይ በ36 ክልሎች ተደራጅታለች።
============================================
2. ካናዳ፣ 
ካናዳም የፌዴራል ኣስተዳደር መዋቅር የሚትከተልና በፕሮቫይንስ የተደራጀች ሀገር ናት። በመጀመሪያዎቹ ዓመታት 4 ክፍላተ ሀገራት የነበሩ ሲሆን በሂደትም ሌሎች በርከት ያሉት ተደራጅተዋል፣ በዚህም መሠረት ባሁኑ ጊዜ በ13 ክፍላተ ሀገራት ተደራጅታልች። በክልል ዙሪያ የሚነሱ ጥያቀዎችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ምላሽ በመስጠት ትደነቃለች።
==========================
3. ናይጄሪያ፣ 
ናይጄሪያ ከኣፍሪካ ትልቋ የፌዴራል ሀገር ተደርጋ ትወሰዳለች። የመጀመሪያዎቹ የክልል ምሥራቾች 3 ሲሆኑ ሀገሪቱ በየወቀቱ ባስተናገደቻቸዉ የፖለቲካ ሂደቶች ምክንያት ክልሎች ወደ 12 ከፍ ብለዋል። በሂደትም በ1976 29 ደረሱ፤ በ1987 30፤ ከዚያም በሕኃላ ከ1990ዎቹ በኃላ ወደ36 ሊያድጉ ችለዋል። 
===============================================
4. ዩናይትድ ስቴትስ
ዩናይትድ ስቴትስ በታሪክ ቀደምት የፌዴራል ስርኣት የገነባች ሀገር ናት። ፌዴረሽኑን የመሰረቱት የመጀመሪያዎቹ ክፍሎች 13 ሲሆኑ ይህም በተለያየ ጊዜ በተላለፉ ዉሳነዎች ቁጥሩ ከፍ ብሎ በኣሁኒ ጊዜ 52 ያህል ክልላዊ መንግስታት ይገኙባታል።
===============================================
የኢትዮጵያ ፌዴራል ሥርዓት፣

በህገመንግስቱ መሰረት የኢትዮጵያ ፌዴራል ሥርዓት በ9 ክልሎችና በ1 ከተማ ኣስተዳደር የተዋቀረ ነው። ክ80 በላይ ብ/ብ/ሕዝቦችና ብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች ባሉበት ሀገር ዘጠኝ ክልሎች ብቻ በቂ ኣለመሆናቸዉን ለማየት ይቻላል። ለዚህም መፍትሔ እንዲሆን በህገመንግሥቱ ኣንቀጽ 47 (፫) ሥር ክልል የመመስረት ስነስርኣት ተቀምጠዋል። በዚህም መሠረት የራሳቸዉ ክልል ያላገኙና በሌሎች ክልሎች ዉስጥ የታቀፉ ብ/ብ/ህዝቦች የራሳችዉን ክልል ማቑቑም እንደሚችሉ ተድንግጓል። ይህም ኣሠራር በብዙ ፌዴራል ሥርዓት በሚከተሉ ሀገሮች ዘንድ የተለመደና የመንግስታት መዋቅር መለዋወጥን ታሳቢ ያደርገ ነዉ።

የሲዳማ ሀዝብ ጉዳይ፣
============================
የሲዳማ ሀዝብ ላለፉት በርካታ ዘመናት ጭቆናን ለማስወገድና የራሱን ጉዳይ በራሱ ለማስተዳደር እልህ ኣስጨራሽ ትግል ኣድርጓል። ኣዲሱ ህገመንግስታዊና ፌዴራላዊ ሥርዓት ሲዘረጋም በህገመንግስቱ መሠረት መብቱ እንዲከበርለት በሠላማዊ መንገድ ታግሎኣል። በሂደቱም በርካታ ዋጋ ከፍሎኣል፣ ልጆቹን ገብሮኣል።

በ1997 ዓም የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ጥያቄውን ኣጽድቆ የራሱን ክልል መንግስት ለማቋቋም ሞክሮ በነበረዉ ጫና እና ኣፈና ሳቢያ ሳይሳካ የቀረ ሲሆን ይህም ክስተት የሀገሪቱ ገዥዎች ምን ያህል ከህገመንግሥቱ በላይ መሆናችዉን ፍንትው ኣድርጎ ያሳየ ክስትተ ሆኖ ኅለፚል። በኣሁኑ ወቅት ክልል የመመስረት ጉዳይ ብዞኑ ምክር ቤት በሙሉ ደምፅ ፀድቆ ለተግባራዊነቱም ህዝቡ ድእልህ ኣስጨራሽ ሠላማዊ ትግል በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በዚህ ወቅት ለማየት የሚቻለዉ፣ የደቡብ ኣንድነትንና የኢትዮጵያ ኣንድነት እንሰብካለን የሚሉ ወገኖች የህዝቡን ህገመንግስታዊ ጥያቄ መልክ ለማሳት ከፍትኛ ደባ እየሠሩ ናቸዉ። ከላይ በኣጭሩ ይቀረበዉ የሌሎች ሀገር ተሞክሮ የራስን ክልል መጠየቅ ጠባብነት እንዳልሆን፣ ነገር ግን መጀመሪያ በህገመንግስቱ ያልተፃፉ ክልሎችን ብጊዜ ሂደት መጨመር የዓለም ተሞክሮ የሚያሳይ መሆኑን፣ በተግባርም የታየ እና ዉጤት ያስገኘ መሆኑን ያሳያል። 
=========================================
በመጨረሻም የኢህኣዴግ እና የደኢህዴን ምክር ቤት የሲዳማ ህዝብ ክልል ጥያቄን ተቀበለ በተባለዉ ላይ፤
=============
ተደጋግሞ እንደተገለፀዉ፣ ህገመንግስታዊ መብቶች ያለማንም ከልካይነት ተግባራዊ መሆን የሚገባቸዉ ናቸው። በመሆኑም ማንኛውም መንግስታዊ ኣካል ተግባራዊነቱን እንዲያረጋግጥ ግዴታ ተጥሎበታል። በዚህም መሠረት ቀደም ባሉት ጊዜዎች በመንግስታዊ ኣገዛዞች ህገመንግሰቱን ካለማክበራችዉ የተነሳ ይህ የቆየ ጠያቄ ተገቢ እልባት ሳያገኝ ቆየ።

ከዚህ ኣንጻር፣ በዶክተር ኣብይ ኣህመድ የሚመራዉ ኢህኣዴግ ምክር ቤት ጥያቄን መቀበሉ በበጎ ጎን የሚወሰድ ነዉ። ቀደም ባሉት ጊዜያት ጥያቄውን ብምክር ቤት መቀበል ቀርቶ መጠየቅና መደገፍም ብርቱ ቅጣት ያስከትል ነበር። የጥቂት ፀረሠላም ኣጀንዳ ነው ይባልም ነበር። ለነገሩ ጥያቄው የሁሉም ሲዳማ ህዝብ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትሩ በሀዋሳ ከተማ ከሲዳማ ህዝብ ጋር ባካሄዱት ውይይት ኣረጋግጠዋል። ከዚያ ወዲህም ሠላማዊ ትግሉ ተቀጣጥሎ ወደማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሶኣል። ደኢህዴን የተሰኘው ግዑዝም ጥያቄውን ለመቀልበስ ያልፈነቀለው ድንጋይ ኣልነበረም። ኣልተሳካለትም እንጂ።

ሆኖም በመንግስት ድረጃ የተደረገዉ ዉይይት ኣስፈላጊ ነዉ። Anthony C. Gilliland (2013). Federalism and the Creation of New States : Justifying the Internal Succession በሚለዉ ሥራቸው ..the process of new state creation is negotiated between the demanding people, the existing entity they belong and the federation as a whole ሲሉ ይመክራሉ። በኣጭሩ፣ ይህ ኣዲስ ክልል የመመስረት ሂደት በጠያቂው ህዝብ፣ ቀድሞ በነበረ ክልል እና በፌዴረሽኑ ወይም ሀገሪቱን በሚመራዉ መንግስት መካከል በጋራ ተነጋግሮ ሀገመንግስታዊ ምላሽ ማስገኘት ያስፈልጋል ሲሉ ይመክራሉ።
================================

ስለሆነም፣ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ህገመንግስታዊ መሆኑን፣ መጀመሪያ ያልነበሩ ክልሎች በሂደት እየተፈጠሩ መሄዳቸዉ በሌሎች ሀገሮችም የተለመደ በምመሆኑ ለኢትዮጵያ ብቻ የተጋረጠ ኣደጋ ኣድርጎ ማቅረቡም የተሳሳት ምልከታ መሆኑን መረዳት ያሻል።

የሲዳማ ህዝብ ክልላዊ መንግስት በቅርቡ እውን ይሆናል።