Gudumaale

   Sidaamu Daga Budu Battala
Connecting Sidama People

የሀዋሳ ከተማ መስፋፋት የመሬት ወረራና የሲዳማ ብሄር እጣ ፋንታ

By Worena Woram'e

መግቢያ
መሬት ለሰው ልጆችና ለሌሎች ፍጡራን መኖሪያነት ፈጣሪ በችሮታው የለገሰው ሀብት ነው፡፡ ይህ ውድ ስጦታ (መሬት) የሰው ልጆች የተሰሩበት፣ ሰርተውና ደክመው ህይወታቸውን የሚመሩበትና የዚህን ዓለም ኑሮ ሲያጠናቅቁ የሚያርፉበት ማረፊያቸውም ነው(……..ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ/ደክመህ/ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህና)።
መሬት ከሰው ልጆች ጋር ያለው ቁርኝት ከመተደዳሪያና ከመቀበሪያ ቦታነት ያለፈ ትርጉም ያለው ነው፡፡ ይኸውም የሰው ልጆች ዝርያ የመቀጠል (Persistence of generations) እና የህዝብ ማንነት ተጠብቆ የመቆየት ጉዳዮች ከመሬት ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው መሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም አንድን ህዝብና የህዝቡን ቋንቋ፣ ባህል፣ የአኗኗር ዘይቤና ማህበራዊ መስተጋብር ከመሬት ነጥሎ ማየት የማይታሰብ መሆኑን ለመረዳት የኑዩክሊየር ሳይንስ አይሆንም::
ይህ ጽሁፍ ከምኒሊክ ጀምሮ በደቡብ፣ በምስራቅና በምዕራብ ኢትዮጵያ ያለዉን የመሬት ወረራ በመዳሰስ በተለይም በአሁኑ ሰዓት በፊንፊኔና በሀዋሳ ከተማ ወያኔ/ደኢህዴን ዘመን በተካሄደው የመሬት ወረራ በሲዳማ ብሔር ቋንቋ፣ ባህልና ዕሴት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳደረ መሆኑን ይተነትናል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ አካባቢ በተካሄደው የመሬት ወረራ በፊንፊኔ አካባቢ የሚኖሩና የኦሮሞ ብሔር አባላት የሆኑት አብቹና ገላን ጎሳዎች ማንነታቸውን ብቻ ሳይሆን ህልውናቸውን ጭምር ያጡበትን ሁኔታ በተመለከተ በጥናት የተረጋገጠ እውነታ በጽሁፉ ውስጥ የቀረበ ሲሆን በተጨማሪም በሐዋሳ ከተማ ማስፋፋትና በኢንዱስትሪ ልማት ስም ወያኔ እየተገበረ ባለው የመሬት ወረራ ምክንያት የሲዳማ ብሔር አባል በሆነው የሀዌላ ጎሳ ላይ የተደቀነውን የመጥፋት አደጋ እንዲሁም በቀጣይ 30 ዓመታት ለመተግበር በወጣው የሀዋሳ ማስተር ፕላን መሠረት በሀዋሳ ዙሪያ (ዶሬ ባፋኖ)፣ በወንዶ ገነት፣ በቦርቻና በከፊል ሸበዲኖ አካባቢ በሚኖሩ ሌሎች የሲዳማ ብሔር ጎሳዎች ላይ ያንዣበበውን የመፈናቀልና የማንነት መጥፋት አደጋ በዝርዝር ማስረጃ ተደግፎ የቀረበ ሲሆን ይህንን የመሬት ወረራና በህዝባችን ላይ የተደቀነውን የማንነት መደብዘዝና መጥፋት አደጋ ከመከላከል አንፃር የተለያዩ አካላት ምን ዓይነት ሚና መጫወት እንዳለባቸው ተመልክቷል፡፡
የከተማ መስፋፋት (Urbanization) እና የመሬት ወረራ
የሰው ልጅ ከጥንታዊና ኋላ ቀር የጋርዮሽ አኗኗር (Primitive Communal Society) እየተላቀቀና በዕውቀት፣ በአመለካከትና በቴክኖሎጂ እየተሸጋገረ ሲመጣ በተበታተነ አኗኗር ራስን ከጠላት ጥቃት መከላከልና ስልጣኔን ማፋጠን እንደማይቻል ለመረዳት በመቻሉ በአንድ አካባቢ ተሰባስቦ ደህንነቱን በጋራ መጠበቅና መሠረታዊ ፍላጎቶቹን በቀላሉ ማግኘት የሚችልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ማሰብ ጀመረ፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ዘመናዊ የማምረት ሂደት (Industrialization) እየተለመደና እየጎለበተ ሲመጣ ለዚህ የሚያስፈልገውን ጥሬ ሀብትና የሰው ኃይል የማፈላለግና የማንቀሳቀስ ስራ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ተሸጋግሮ ስለነበረ ብዙ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችና ሰራተኞቻቸው በአንድ ቦታ እየተሰባሰቡ የመጡበት ሁኔታ ነበር፡፡ በዚህ መልኩ ህዝብ፣ የአገልግሎት ተቋማትና የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች አንድ ላይ ተሰባስበው መንደሮች እየሆኑና እየሰፉ በመሄድ ዛሬ ከተማ ተብለው የሚጠሩ አካባቢዎችን ለመፍጠር በቁ፡፡
ይሁንና በዓለማችንም ሆነ በኢትዮጵያ የከተማዎች አመሰራረትና ዕድገት ፍትሐዊነት የጎደለውና ሁለት መልክ ያለው መሆኑን ማየት ያስፈልጋል፡፡ ዓለም አቀፋዊውን ሁኔታው ስንመለከት ብዙ ከተሞች የተፈጠሩት በቅኝ አገዛዝ ወቅት ነበር፡፡ በተለይም ከ17ው ክ/ዘመን ጀምሮ አውሮፓውያን አሳሾችና ቅኝ ገዥዎች ከወትሮው በተለየ መልኩ መሬትንና በውስጧ ያለውን ሀብት ለመበዝበዝ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ ስለነበረ ብዛት ያለውን የዓለም ክፍል በተለይም አፍሪካን በቁጥጥራቸው ስር ማድረግ ችለዋል፡፡ ይህ የአውሮፓ ኃይል አፍሪካንም ሆነ ሌሎች የዓለምን ክፍል በመሳሪያ ጡንቻ በተቆጣጠረበት ወቅት በየአካባቢው ለራሱ ምቹ መኖሪያነት የሚሆኑ ከተማዎችን ይመሰርት ነበር፡፡ እነዚህ ከተሞች የንፁሀን ህዝብ ደም የሚፈስባቸው፣ የጦርነት ዕቅዶች የሚነደፍባቸው፣ ሰብዓዊ መብቶች የሚጣስባቸው፣ የህዝብ ማንነት የሚንቋሸሽባቸውና በኃይል ወይም በመቀየር አካሄድ (conversion) ማንነትን የማጥፋት ስራ የሚሰራባቸው ከመሆናቸውም በላይ የተዘረፉ ጥሬ ሀብቶች ወደ ፋብሪካ ምርትነት የሚለወጡባቸው ወይም ወደ አውሮፓ ሀገሮች ለማሸጋገር ዝግጅት የሚደረግባቸው ቦታዎች ነበሩ፡፡ በዚህም ምክንያት በአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች የተመሠረቱ ከተሞች ለመጤው ሰፋሪዎች (ለአውሮፓውያን) የተደላደለ ኑሮ የሚያቀርቡና ለነባሩ ህዝብ /ለመሬቱ ባለቤቶች/ ምድራዊ ሲኦል የሆኑ ነበሩ፡፡ በተቃራኒው ግን አውሮፓውያኑ በራሳቸው ሀገር የፈጠሯቸው ከተሞች የራሳቸው ህዝብ ከነሙሉ መብታቶቻቸውና ማንነታቸው ጋር ተከብረው የሚኖሩባቸው የሰው ልጆች መኖሪያ ናቸው፡፤
በኢትዮጵያም የከተሞች አመሰራረትና ዕድገት ከዚህ የተለየ ገጽታ የለውም፡፡ እውነተኛ የታሪክ መዛግብቶች እንደሚያሳዩት ከ19ኛው ክ/ዘመን በፊት ኢትዮጵያ የሚባል ሀገር አልነበረም፡፡ ከዚህ ዘመን ቀደም ብሎ አሁን ወደ ኢትዮጵያ የተጠቃለሉ ሁሉም ህዝቦች (ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣ አጌው፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ሀዲያ…ሌሎችም) የየራሳቸው የመንግስት ስርዓት የነበራቸው ነፃ (በቅኝ ያልተገዙ) ህዝቦች ነበሩ፡፡ በእነዚህ ነፃ ህዝቦች ጎን /በጎረበትነት/ በመሳፍንቶች የስልጣን ሽኩቻ ምክንያት የተፈረካከሰ የአቢሲኒያ ሀገር (አማራና ትግሬ) ነበር፡፡ በመሠረቱ ሀበሻ የሚለው ቃል ሀበሻት ከሚለው ቃል ተሻሽሎ የተወሰደ ሲሆን ይህም በጥንት ዘመን (ከ3000 ዓመታት በፊት) ከአጋዚያን ነጋዴዎች ጋር ከደቡባዊ አረቢያ ተነስተው በኩሽ ሀገር መጥተው የሰፈሩትንና በኋላም ወደ አማራነትና ትግሬነት የተከፋፈሉትን ህዝቦች የሚገልጽ ቃል ነው፡፡ የሀበሻ “ታሪክ ፀሐፊዎች” (ደብተራዎች) ኢትዮጵያ የ3000 ዓመታት ታሪክ አላት ብለው ሲጽፉ እነሱ በኩሽ ህዝቦች መካከል መጥተው ከሰፈሩበት ቀን ጀምሮ ያለውን ሁኔታ ለመግለጽ ካልሆነ በቀር የዛሬይቷ ኢትዮጵያ ከ100 ዓመታት የዘለለ ታሪክ የላትም፡፡ እነዚህ የሀበሻ ህዝቦች(አማራና ትግሬ) ከሌላ አካባቢ ፈልሰው እንደመጡ ገለልተኛ የውጭ ሀገር የታሪክ ምሁራን ጭምር የፃፉ ቢሆንም የራሳቸውን ታሪክ ቀይረው የመሬቱ ባለቤት የሆኑትን የኩሽ ምድር ሀዝቦች (ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ ሀዲያ፣ ካምባታ፣ ጌዴኦ፣ ጣምባሮ፣ ሀላባ….) በፍልሰት የተስፋፉ ናቸው ብለው ሲጽፉ የዝንጀሮ ጭንቅላት እንኳ እንደሌላቸው መታዘብ ይቻላል፡፡
ወደ ዋናው ጉዳይ እንመለስና በ19ኛው ክ/ዘመን የአቢሲኒያ (የአማራና የትግሬ) ነገስታት በክርስትና ኃይማኖት ስም ከአውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች ጋር በመቀራረብ በአካባቢያቸው የእስላሞች እንቅስቃሴ እንዳስቸገራቸው ይገልጹና ይህንንም ተቆጣጥረው የክርስትና ኃይማኖትን (የአብሲኒያ ኦርቶዶክስን) ማስፋፋት እንዲችሉ የጦር መሳሪያ እርዳታ እንዲሰጠቸው ጥያቄ ያቀርቡ ነበር፡፡ ጥያቄያቸውም ተቀባይነት አግኝቶ (አውሮፓውያኑ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ ለማሳካት ሲሉ) ለቁጥር የሚታክት የጦር መሳሪያዎች (ከሁለት መቶ ሺ በላይ የተለያዩ ጠብ-መንጃዎችን) በተለያዩ ክልሎች በመሳፍንት ተበጣጥሰው ሲገዙ ለነበሩ የአቢሲኒያ ገዥዎች እጅ ሊገባ ችሏል፡፡ ከእነዚህ የአቢሲኒያ ነገስታት መካከል ጎልቶ የወጣው አፄ ምኒልክ (የመንዝ ወይም የሸዋ አማራ ገዥ) ነበሩ፡፡ ይህ የአውሬ አስተሳሰብ የነበረው ሰው ከአውሮፓውያኑ ጋር በጥቅም ዙሪያ ብዙ ውሎችን ይፈራረም የነበረ ሲሆን ለውለታውም ከፍተኛ የጦር መሳሪያዎችን ሲያገኝ ስለነበረ መላውን ኦሮሞ፣ ሲዳማና ሌሎች የደቡብና የአሁኗ ኢትዮጵያ ህዝቦችን በቀላሉ በቅኝ ገዥነት ለመቆጣጠር አስችሎታል (በመሠረቱ ምኒልክ ከኢጣሊያ ጋር ወደ ጦርነት የገባው በጥቅም ዙሪያ የተዋዋለውን ውል ማክበር ባለመቻሉ እንደሆነ ግልጽ ነው)፡፡ በወቅቱ እነዚህ በምኒልክ ቅኝ ግዛት ስር የወደቁ ህዝቦች ከፍተኛ የመከላከል ተጋድሎ ያደረጉ ቢሆንም የያዙት መሳሪያ ባህላዊ ጦርና ጋሻ ብቻ ስለነበረ አውሮፓ ሰራሽ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ከያዘና በምኒልክ ከተመራው የአማራ ቅኝ ገዥ ኃይል ራሳቸውን ማዳን ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡
በዚህ መልኩ የህዝቦችን መሬት በኃይል በቁጥጥሩ ስር ያስገባው የአማራ ቅኝ ገዥ መደብ በየቦታው ለቁጥጥር የሚመቹት ቦታዎችን መርጦ ከተማ ያደርግ ነበር፡፡ በእነዚህ ከተሞች የመሬት ባለቤቶች የሆኑት ነባሩ ህዝቦች/ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣…/ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ እንስሳ ከመታየታቸውና በራሳቸው መሬት ላይ የበይ-ተመልካች ከመሆናቸውም በላይ ማንነታቸውን እንዲጠሉና ሞራላቸውን እንዲያጡ የሚያደርጉ ጭቆናዎችን አስተናግደዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም እጆቻቸውና ጡቶቻቸው ተቆርጧል፣ በግፍ ተጨፍጭፈዋል፣ ሀብታቸው ተዘርፎ ለነፍጠኞቹ መደለቢያ ሆኗል፡፡ ከዚህ በተለየ መልኩ ግን በሰሜን አካባቢ የነበሩ ከተሞች በራሳቸው በአቢሲኒያውያኑ (በአማራና በትግሬ) ቁጥጥር ስር የነበሩ በመሆናቸው በህዝቦቹ ላይ ይህ ነው የሚባል ረገጣ አልደረሰባቸውም፡፡ ለዚህም ነው የአውሮፓና የኢትዮጵያ ከተሞች ተመሳሳይና ሀሉት ገፅታዎች አላቸው ያልነው፡፡
በአውሬው ምኒልክ ጠንካራ መሠረት ተጥሎለት የነበረው የአቢሲኒያ የመስፋፋት ሂደት በኃይለስላሴ ዘመንም ተጠናክሮ በመቀጠል የህዘብን መሬት እየነጠቀ ለነፍጠኛውና ሲሶውን ደግሞ ለኦርቶዶክስ ቤተ-ክርቲያን የማውረስ ተግባሩን ተያያዘበት (በነገራችን ላይ የኃይለስላሴ ወይም የተፈሪ አባት የሆኑት መኮንን ወልደሚካኤል ጉዲሳ በምኒልክ ዘመን የሀረር ገዥ የነበረ ሲሆን የዘር ሐረጉም ከኦሮሞ የሚመዘዝ ነው፡፡ ሆኖም እሱም ሆነ ልጁ ኃይለስላሴ በሙሉ አስተሳሰባቸውና ተግባራቸው አማራይዘሽን ያጠቃቸዉ ስለነበሩ የኦሮሞን ህዝብ ይጨቁኑ ነበር)፡፡ በዚህም ምክንያት ነባሩና የመሬት ባለቤት የሆነው ህዝብ የነፍጠኛው ጭሰኛና አገልጋይ ሆኖ ከመቀጠሉም በላይ በመሬቱ ላይ በተመሠረቱ ከተሞች ውስጥ ምንም ይዞታ የሌለውና በእግሩ እንኳን ከተማ ገብቶ ሲረግጥ የሚሸማቀቅ ነበር፡፡
የአፄዎቹ ታሪክ በ1966/67 በፈነዳው ህዝባዊ አብዮት ወደ መቃብር ሲወርድ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ወደ ስልጣን የመጣው የደርግ (የኢሠፓ) ወታደራዊ መንግስት መሬትን ወደ ባለቤቶቹ ለመመለስ የወሰደው እርምጃ የሚደነቅ ነበር፡፡ ደርግ (በመንግስቱ ኃይለማርያም የሚመራው ኮሚቴ) መሬት ለአራሹ የሚለውን ፖሊሲ በማውጣት መሬቱ ተነጥቆ ለነበረው ጭቁኑ ህዝብ መሬቱን ከመመለሱም በላይ የነፍጠኛውን አከርካሪ እንደገና ማገገም በማይችል ደረጃ አድቋል፣ ጭቁን ህዝብም ነፍስ እንዲዘራ አድርጓል፡፡ በርግጥ የደርግን መንግስት የሚዘውሩ ቡድኖች/Steering Groups/ አብዛኛዎቹ የፍዉዳሉ ርዝራዦች ስለነበሩ የዘር ሐረጉን ወደ ኦሮሞ የሚመዘውን ፕሬዝደንት መንግስቱ ኃይለማርያምን ክፉኛ ተፈታትነውታል፡፡ በዚህም ላይ ላዩን የሥርዓቱ ደጋፊዎች ሆነው ውስጥ ውስጡን ግን ሰውዬው የእኛን ህዝብ ወደ ማጥቃት እየተሸጋገረ ነው በማለት በህቡዕ ይመካከሩና ተቃዋሚዎችን ያደራጁ ነበር፡፡ እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት አንድ ምስጢር መንግስቱ ኃይለማርያምን ወደ አምባገነንነት ያሸጋገረው ጉዳይ ራሳቸውን ከእስራኤል ወገን እነደመጡ አድርገው በከንቱ የሚያምኑ የሸዋዉ የነፍጠኛዉ ተወላጆች ሰውዬውን ከሰለሞን የዘር ግንድ ውጪ ስለሆ ስልጣን ላይ መውጣት የለበትም በማለት ለጥቃት ሲዘጋጁ ስለደረሰባቸው እንደሆነ በቅርቡ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የሆነ ሆኖ በመንግስቱ ኃይለማርያም የሚመራው መንግስት አምባገነናዊ ባህሪይ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ ያደረገው ቢሆንም የገጠሩን መሬት ለባለቤቶቹ በመመለስ፣ በከተማም ነባሩ ህዝብ ሳይሸማቀቅ ገብቶ እንዲወጣ ከማድረግ ባለፈ እንደማንኛውም ወራሪ ነፍጠኛ በከተማ መኖሪያ ሠርቶ መኖር መብቱ እንደሆነ በማስተማር፣ በከተማዎች መስፋፋት ስም መሬት ከድሀው እጅ እንዳይነጠቅ በማድረግና የጭቁን ህዝብ ልጆች ዘመናዊ ትምህርት እንዲማሩ በማበረታታት መንግስቱ ኃይለማርያም ከአቢሰኒያ ፊውዳሊስት ገዥዎች እጅጉን የተለዩ መሪ ነበሩ፡፡ ከዚህም ባሻገር በአማራው ቅኝ ገዥዎች አማካይነት በኃይል አንድ እንዲሆኑ የተገዳዱ ህዝቦችን በውስጧ የያዘችው ኢትዮጵያ ሳትበታተን እንዲትቆይ መንግስቱ ኃይለማርያም ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ እዚህ ላይ የአቢሲኒያ ዝርያ ያላቸው ገዥዎች ለኩሽና ለሌሎች የኢትዮጵያ የዘር ግንዶች ምን ያህል ንቀት እንዳለባቸው የሚያሳየውን አንድ ነገር ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ የእንስሳት ጭንቅላት ያለው ምኒሊክ የኦሮሞን፣ የሲዳማን፣ የሶማሌን.... ሌሎች ህዝቦችን ኢሰብዓዊ በሆነ መልኩ በመጨፍጨፍ ኢትዮጵያን ስለመሰረተና እንግሊዞችና ፈረንሳዮች ምስራቅ አፍሪካ በኢጣሊያ ቁጥጥር ስር እንዳይወድቅ በመፈለግ ለኢትዮጵያ የጦር ድጋፍ በማድረጋቸው ኢጣሊያን በአድዋ በማሸነፉ የኦሮሞ ምድር በሆነው ፊንፊኔ (አዲስ አበባ) ላይ ሐውልት ቆሞለታል፡፡
ታዲያ በምኒሊክ የተጨፈጨፈው የኦሮሞ፣ የሲዳማ፣ የጌዲኦና የሌሎች ህዝቦች ደምና አጥንት የሰው ዘር ደምና አጥንት ስላልሆነ ነው ለጨፍጫፊ ምኒሊክ በፊንፊኔ ሐውልት የቆመለት? ወይስ መንግስቱ ኃይለማርያም በዘር ኦሮሞ ስለሆነ ነው ሐውልት የማይቆምለት?
የሆነ ሆኖ የደርግ መንግስት ከዘመኑ ጋር መራመድ ትቶ የሶሻሊዝም ርዕዮትን የሙጥኝ ብሎ በመያዙና ይህንን ርዕዮት በበላይነት ይመራ የነበረው የሶቪዬት ሶሻሊስት መንግስት በመፈረካከሱ አጋጣሚው በምዕራባውያን በተለይም በአሜሪካ ድጋፍ ጫካ ገብተው የጉሬላ ውጊያ /Guerilla warfare/ ሲያካሂዱ ለነበሩት የወያኔ ቡድኖች (ለሕወሀትና ኢህዴን/ መልካም ሁኔታ ፈጠረላቸውና ስልጣን ለመያዝ በቁ፡፡ በመሠረቱ ደርግ የተሸነፈው በአንድ በኩል የማንነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን መመለስ ባለመቻሉ አብዛኛው ህዝብ ጀርባውን ስለሰጠው ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የሶሻሊዝም ካምፕ በመፈረካከሱ ነዉ፡፡
በ1983 ደርግ ከወደቀ በኋላ የመንግስትን የስልጣን ወንበር የተቆናጠጠው የወያኔ ቡድን በመግቢያው አካባቢ ዲሞክራሲያዊና ለሕዝብ መብት የታገለ ድርጅት የሚያስመስሉ ተግባራትን ማከናወን ጀምሮ ነበር፡፡ ለአብነትም የኤርትራ ሕዝብ የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው እንዲወስንና በሪፈሬንደም እንዲገነጠል ማድረጉ (ምንም እንኳን የአፋሮችን ወደብ ለኤርትራ አሳልፎ በመስጠት ሀገርቷን ጭምር የባህር በር ያሳጣት ቢሆንም)፣ ከሌሎች ብሔራዊ ድርጅቶች ጋር ሆኖ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም በማድረግ ሀገርቷን ወደ መረጋጋት ማምጣት መቻሉ፣ ከነጉድለቱም ቢሆን የብሔሮችን ራስን በራስ የማስተዳደርና የማንነት ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችል ህገ-መንግስት በመቅረጽ ብሔረሰቦች የራሳቸውን አስተዳደር (ጥርስ የሌለው ቢሆንም) መመስርትና ማንነታቸውን ማሳደግ ብሎም የእምነት ነፃነነታቸውን ማረጋገጥ እንዲችሉ መልካም እርምጃዎችን በመውሰዱ ቡድኑ የተሻለ ነገር ሳይኖረው አይቀርም የሚል ተስፋ ጭሮ ነበር፡፡
ይሁንና የወያኔ ቡድን (ተላላኪዎቹ የሆኑትን ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴንን ከጀርባ አድርጎ) የወሰዳቸው ተስፋ ሰጪ እርምጃዎች ጊዜያዊና አቅም እስኪያሰባሰብ ድረስ ብቻ እንዲቆዩ አድርጎ የቀረጻቸው ስውር ሴራዎችና ስልታዊ አካሄዶች መሆናቸውን ለመረዳት የተቻለው በጊዜ ሂደት እየፈፀመ በመጣው ኢ-ዲሞክራሲያዊና መሰሪ ተግባራቱ ነው፡፡ ወያኔ በመነሻ አካባቢ መልካም የሚመስሉ የማዘናጊያ እርምጃዎችን የወሰደው በጫካ ቆይታው ወቅት ክፉኛ ተጎሳቁሎና ተደቁሶ ስለነበረ 4 ኪሎ በገባ ማግስት ተጨማሪ ጦርነት ውስጥ ላለመግባትና ሌሎች የቤት ስራዎችን ኃይልና ሀብት ካሰባሰበ በኋላ ለማከናወን አቅዶ ስለነበረ ነው፡፡
በጊዜ ሂደት ወያኔ (የትግሬ ገዥ መደብ) በወታደራዊና በሀብት አቅሙ እየተጠናከረ ሲሄድ በጫካ ውስጥ የወጠነውን ቀመር (Formula) ወደ ተግባር የሚቀየርበትን እርምጃዎች መውሰድ ጀመረ፡፡ በዚህም ዲሞክራሲያዊ መርሆዎችን ወደ መርገጥ፣ የህዝብ ድምፅ ወደ መቀማትና ሰብዓዊ መብቶችን ጭምር ወደ መጨፍለቅ ተሸጋገረ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ከቅድመ-አባቶቹ (ከአቢሲኒያ ገዥዎች) በወረሰው ትምህርት መሠረት የዝርፊያ ስልቱን ወደ ዘመናዊ ቅኝ ግዛትነት ቀይሮ የህዝብን ሀብት በመበዝበዝ ላይ ተጠመደ፡፡ በዚህም ከድንጋይ በቀር ይህ ነው የሚባል የተፈጥሮ ሀብት አይተው የማያውቁትን በርካታ የትግሬ ተወላጆች ከሰሜን ወደ ኦሮሚያ (ፊንፊኔን ጨምሮ) እና ደቡብ አከባቢዎች እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ በወርቅ ፋብሪካዎች፣ በከተማ መሬት ሽያጭና ሪል ኢስቴት፣ በቡና መፈልፈያ ኢንዱስትሪዎች፣ በቆዳና ሌጦ ማቀነባበሪያዎች፣ በባንክና ኢንሹራንስ ተቋማት፣ በህጋዊና ኮንትሮባንድ አስመጪ-ላኪ ንግድ (Import-Export Trade)፣ በማዕድን ውሃና በቢራ ማምረቻዎች፣ በኮንስትራክሽን ሥራዎች፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በመከላከያ አውቶሞቲቭና ሎኮሞቲቪ ኢንዱስትሪዎች፣ በኤለክትሪክ ኃይል ግንባታዎች፣ በቴሌኮሙኒኬሽን አቅርቦት፣ በአየር መንገድ እና በሌሎች ወሳኝ ዘርፎች ሁሉንም ወይም አብዛኛውን አክሲዮን (የድርጅቶቹን የሀብት ድርሻ) ወይም የሥራ ዕድል እንዲይዙና የሀገሪቷን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በቁጥጥራቸው ስር እንዲያደርጉ አድርጓል፡፡ ይህንንም ያለማንም ተቀናቃኝ ማካሄድ እንዲችሉ የመከላከያ ጀኔራሎችንና ሠራዊቱን፣ የፖሊስ ኃይሉን፣ የብሔራዊ ደህንነት ሥርዓቱን፣ የፋይናንስ መረጃና ደህንነት ማዕከላትን፣ የገቢዎችና ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችን እና ሌሎችም ለኢኮኖሚ ቁጥጥር አስፈላጊ የሆኑ የመንግስት ተቋማትን በወያኔ እንዲዋቀር በማድረግ አስተማማኝ ፀጥታ እንዲኖርና ሁኔታዎች ምቹ እንዲሆኑ አድርጓላቸዋል፡፡ ይህ የትግሬዎች የጭቆና መረብ ከቀድሞዎቹ የነፍጠኛዉ/ ፊውዳሎች ሥርዐት የሚለየው በሀገርቷ የብሔሮችና ብሔረሰቦች መብት እንደተከበረ በማስመሰል ህዝቦች በቋንቋ፣ በባህልና በሀይማኖት ላይ በተሰጣቸዉ የቤት ሥራ ላይ እንዲያተኩሩና በጭፈራ እንዲሰክሩ በማድረግ ዓይናቸው ሌሎች ጉዳዮችን ከማየት እንዲታወር ተደርጎ እየተፈፀመ ያለ ፀጥተኛ ግድያ (Silent Killing) በመሆኑ ነው፡፡ ለመሆኑ የብሔሮች መብት የሚባለው ጭፈራ ብቻ ነውን? የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ለእነዚህ ህዝቦች አይገባችውምን?
የወያኔ መንግስት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሥርዓቱን ሙሉ በሙለ ከመቆጣጠር ባለፈ ቀደምት የአቢሲኒያ ዘመዶቹ ያካሄዱትን የመሬት ዘረፋ በዘመናዊ አሰራር አጠናክሮ በመቀጠል ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም በኦሮሞና በሲዳማ ህዝቦች መሬት ላይ የሚካሄደው ቅሚያ እጅጉን የከፋ ሲሆን በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል-ጉሙዝ፣ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በቤንች ማጂ፣ በሻካ፣ በደቡባዊ ኦሞ እና በሌሎች አካባቢዎችም መሬት በግፍ ከባሌቤቶቹ እጅ ወጥቶ ወደ ትግሬ-አማራ-ጉራጌ (ትግሬ እና ከትግሬ ጋር የተዋሃደ ) እጅ እንዲገባ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ለዚህም ከህገ-መንግስት ጀምሮ በየጊዜው የተለያዩ ህጎችንና ፖሊሲዎችን ይቀርፃል፣ እጅ በሚያነሱ አሻንጉሊቶች በተሞላ ፓርላማ አማካይት እንዲፀድቅ ያደርጋል፣ ይተገብራል፡፡ አንዳንዴ ወደ ፓርላማ ማቅረብ ሳያስፈልግ በወያኔ የበላይነት በሚመራ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቀው ስራ ላይ የሚውሉ ህጎችና ፖሊሲዎች አሉ፡፡
የወያኔ ቡድን ለመሬት ቁጥጥር እንዲያመቸው ያወጣቸውን ህጎችና ፖሊሲዎችን መመልከቱ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ምልከታውን ከህገ-መንግሰት ስንጀምር በ1987 በብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ስምምነት ፀድቋል ተብሎ በስራ ላይ የዋለው ህገ-መንግስት አወዛጋቢ የመሬት ድናገጌዎችን የያዘ ነው፡፡ ለምሳሌ "አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 3 የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ ነዉ፡፡ መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነዉ" በአንድ በኩል የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ህልውናና ማንነት መሠረቱ መሬት መሆኑን የሚገልጽ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ መሬት የመንግስት መሆኑን የሚደነግግ አንቀጽ ይገኝበታል፡፡ በመነሻው ሲገለጽ እንደነበረው መሬት የመንግስት እንዲሆን የተደረገው ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ከድሀው እጅ መሬት እንዳይነጥቁ ነው፡፡ ይህ ማሳመኛ በርግጥም ትክክለኛ አስተሳሰብ ነው ብለን ተቀብለን ኖረናል፡፡ ሆኖም ወያኔ ምስጢራዊውን ዕቅድ ወደ ተግባር በቀየረባቸው ዓመታት የወሰዳቸውን እርምጃዎች ስንመለከት እምነታችን ልክ አልነበረም፡፡ ለአብነትም በ2004 ዓ.ም የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተላለፍ የወጣው አዋጅ ማንኛውም የመኖሪያና የቢዝነስ ቦታ የሚሰጠው በጨረታ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ አዋጁ ይህንን ከማስቀመጥ ባለፈ የአካባቢው ብሔር በመሬቱ ላይ ከሚመሰረተውና ከሚስፋፋው ከተማ ምን የተለየ መብትና ጥቅም ያገኛል? ከተማው እየተስፋፋ ሲሄድ የህዝቡ ማንነት እንዴት ይከበራል? አንድ ግለሰብ በአንድ ከተማና በአጠቃላይ በሀገርቷ ባሉ ከተሞች ውስጥ ስንት ይዞታዎች ይኖሩታል? የሚሉ ጥያቄዎችን አይመልስም፡፡ በመሰረቱ የጨረታ አሰራር መሬትን በአግባቡ ለማስተዳደር የሚጠቅም ከመሆኑም በላይ ከተማው ከጨረታ የሚያገኘውን ገቢ በመጠቀም አስፈላጊውን መሰረተ-ልማት ለህዝቡ ማቅረብ እንዲችል የሚያደረግ በመሆኑ በመርህ ደረጃ ችግር የለበትም፡፡ ችግሩ ግን የወያኔ ህጎችና ፖሊሲዎች ከላይ ሲታዩ እንደ ማር የሚጣፍጡ በውስጣቸው ግን እሾህና መርዝ የያዙ መሆናቸው ነው፡፡ ህገ-መንገስቱም ሆነ እሱን ተከትለው የወጡ ህጎችና ፖሊሲዎች መሬትን ከህዝብ እጅ በቀላሉ ለመንጠቅ የተዘጋጁ እንጂ የምንተማመንባቸው እንዳልሆኑ አሁን ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ እነዚህን ህጎችና ፖሊሲዎች በመጠቀም በግፍ ቢዝነስ ቢሊዬነር የሆኑት የትግሬና ከትግሬ ጋር ውህደት የፈጠሩ የአማራ-ጉራጌ ባለሀብቶች በአንድ ከተማ ውስጥ ብቻ በርካታ ይዞታዎችን በግለሰብ ደረጃ በመሰብሰብ ምንም እሴት ሳይጨምሩ መሬትን በመሸጥ፣ የቢዝነስ ቤቶችን በመገንባትና በማከራየት፣ ሪል እስቴት በሚል ኢንቨስትመንት ስም አንድ ከተማ የሚያህል መሬት በግል አጥረው በመያዝ፣ የመኖሪያ ቤቶችን በመገንባት የአካባቢውን ነባር ተወላጆችና ወደ ከተማ በየጊዜው የሚጎርፉ ነዋሪዎችን በየወሩ በሚጨመሩት የቤት ኪራይ በማሰቃየት በሀብት ላይ ሀብት መቆለል ችለዋል፡፡ በተለይም በፊንፊኔ (አዲስ አበባ)፣ በቢሾፍቱ፣ በሐዋሳ፣ በሰበታ፣ በአዳማ፣ በዓለምገና፣ በቡራዩ፣ በላጋጣፎ-ላጋዳድ፣ በሱሉልታ፣ በድረዳዋ፣ በጂማ፣ በሻሻማነ፣ በአርባምንጭ፣ በዲላና በሌሎች የኦሮሚያና የሲዳማ አካባቢዎች ሁኔታው እጅግ አስከፊ ሲሆን ከአርሶ-አደሩ እጅ መሬት ያለበቂ ካሳ ነጥቆ ለወያኔና ለአጋር ወገን ባለሀብቶች የማስተላለፉ ስራ በህግ ዕውቅና የተሰጠው ሆኗል፡፡
ከሊዝ አዋጁ በተጨማሪ ወያኔ ከህዝብ እጅ መሬትን ለመንጠቅ ሲል በዓይነትና በመጠን የበዙ አሰራሮችን ዘርግቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የመንግስት የቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ፣ ትላልቅ ከተሞችን ከአከባቢያቸው ከተሞችና የገጠር ወረዳዎች ጋር የማቀናጀት ፕላን፣ የከተማ ፕላንና መሬት ማኔጅሜንት ኮርፖሬሽን እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ ወያኔና አጋሮቹ እነዚህን ዓይነተ-ብዙ የመሬት መቀራመቻ ፖሊሲዎችን ከህገ-መንግስቱ ድንጋጌ ጋር እያጣጣሙ የህዝብን መሬት የመንጠቅና በምትኩ አቢሲኒያዎችን የመተካት ተግባራቸውን በስፋት ቀጥለውበታል፡፡ ለአብነትም የቅንጅታዊ ልማት ፕላን አሰራርን በመጠቀም አዲስ አበባን በዙሪያው ካሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞችና ወረዳዎች ጋር ለማዋሀድ የተነደፈው ምስጢራዊ ዕቅድ ወደ ትግበራ ተሸጋግሯል፡፡ ወያኔ ስለ ፕላኑ የሚያቀርበው ሽፋን በፊንፊኔ ዙሪያ ያሉ ከተሞች ከአዲስ አበባ ልማት ተጠቃሚ መሆን አለባቸው የሚል ነው፡፡ ለመሆኑ አዲስ አበባ ከራሱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች /የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ እጦት፣ የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ሥራ አጥነት፣ ቤት-አልባነት፣ የውሃ እጥረት፣ ረሀብተኛነት፣ ጎዳናና ሴተኛ ተዳዳሪነት፣ የቆሻሻ ክምችትና ግማት፣ የመንገድና የትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ችግር፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች ጥራትና ብቃት ችግር፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አቅርቦት ችግር፣…ወዘተ) መቼ ወጥቶ ነው ለሌሎች ከተሞች ልማት የሚለግሰው? እስኪ ከችግር የተላቀቀውን ምናባዊ አዲስ አበባ እናስብና ይህ የብልጽግና ጫፍ የነካ ከተማ በቅንጅታዊ ፕላን ስም በዙሪያው ያሉትን ከተሞች ለመዋጥ ከሚያቅድ ይልቅ እነዚህ ከተሞች በራሳቸው መንገድና ሥልጣን እንዲያድጉ ለምን ካፒታል (ፋይናንስ፣ ማሽኔሪና ኢክዩፕሜንት፣ አቅም ግንባታ) አያቀርብላቸውም? እንደውም ጉዳዩ ለአካባቢው የኦሮሞ ህዝብ ከመጨነቅ የሚመነጭ ነው ብለን እንውሰድና የኦሮሞ ባለሙያዎች በአዲስ አበባ በሚከፈቱ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ለምን አፋን ኦሮሞን ተጨማሪ የሥራ ቋንቋ አድርጎ አይጠቀምም? ስለዚህ በየጊዜው መልካቸውን እየቀያየሩ የሚወጡ የከተማ ልማት አዋጆችና ፖሊሲዎች ለእነዚህ ዓይነት አመክኗዊ (logical) የመብት ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡ አይደሉም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ አዋጆቹና ፖሊሲዎቹ የሚቀረፁት የአካባቢውን ህዝብ ለመጥቀም ሳይሆን የህዝብን መሬት ለመቀማት ተብሎ ነውና፡፡ እነዚህ አጥፊ አዋጆችና ፖሊሲዎች የተፅዕኖ አድማሳቸውን እያስፋፉ ሲሆን በቅርብ ጊዜ በሐዋሳና በሌሎች ከተሞች ተግባራዊ እንዲሆኑ የማስጀመሪያ መመሪያዎች እየተዘጋጀላቸው ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ የጥንቶቹ የአቢሲኒያ ገዥዎች በሀገር-ማቅናት ስም (በኃይል አንድ በማድረግ) መሬታችንን የነጠቁ ሲሆን የአሁኑ የወያኔ መንግስት ደግሞ በከተማ ማስፋፋትና በልማት ስም የኦሮሞ፣ የሲዳማና የሌሎች ህዝቦችን ሰብዓዊና ዲሚክራሲያዊ መብት በመርገጥና በርካታ ህይወቶችን በማጥፋት መሬታቸውን እየነጠቀ በቦታው የራሱን ወገን የመተካት ስራ እየሰራ ነው፡፡ ስለዚህም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፍትሐዊ የከተማ ልማትና መስፋፋት (urbanization) ሳይሆን የመሬት ወረራና የኢኮ-ፖለቲካል የበላይነት ለማረጋገጥ የሚካሄድ ዘመናዊ የግዛት ማስፋፋት /Neo-imperialism/ መሆኑን በግልጽ ማየት ይቻላል፡፡

አዲሱ የግዛት ማስፋፋትና የህዝቦች ማንነት ዕድል ፈንታ
/Neo-imperialism & the fate of peoples’ identity)

የከተማ መስፋፋት (Urbanization) የሰው ልጆች በህይወት ዘመናቸዉ ከሚያስተናግዷቸውና መግታት ከማይችሏቸው ክስተቶች (Inevitable occurences) አንዱ ሲሆን ሂደቱ የህዝቡን ባህል፤ እምነት ቋንቋ፣ እሴትና ሰብዓዊ መብት በማይነካ መልኩ ከገጠር ምናልባትም ከኋላ-ቀር የአኗኗር ዘይቤ ወደ ምቹ የከተማ ኑሮና ስልጣኔ የሚደረግ ሽግግር መሆኑን አይተናል፡፡ ከዚህም ባሻገር የከተማ ዕድገትና መስፋፋት የሚባለው የብሔሮች ራሳቸዉን በራሳቸዉ የማስተዳደር መብት ሳይነጠቅና በመሬት የቡድን ባለቤትነት (Group ownership of land) ላይ እምብዛም ለውጥ ሳይኖር በነባሩ ህዝብ ቁጥጥር ውስጥ ሆኖ የሚመጣ አዎንታዊ ለውጥ ነው፡፡ ከዚህ ዉጭ የሚከናወን የከተማ መስፋፋት አካሄድ የከተማ ፕላንና ልማት ምሁራን እንደሚሉት የከተማ ልማት ሳይሆን የመሬት ወረራና ፀጥተኛ የዘር ማጥፋት ሴራ (Silent Genocide) ነው፡፡
በከተማ ልማትና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ስም በተካሄደው ፀጥተኛ የዘር ማጥፋት ሴራ (Silent Genocide) በዓለምና በኢትዮጵያ ደረጃ ማንነታቸውን ያጡና በአደጋ ላይ የወደቁ ህዝቦች መኖራቸውን በርካታ መረጃዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡

በእኛ ሀገር የሆነውንና እየሆነ ያለውን ሁኔታ ከማየታችን በፊት እስኪ በሌሎች ክፍለ-ዓለም የሆነውን ሁኔታ እንመልከት፡፡ ከ15ኛው እስከ 16ኛው ክ/ዘመን አሜሪካን የደረሱ አውሮፓውያን አሳሾች ሀገሩ ባዶ ሆና አላገኟትም፡፡ ይልቁንስ የህዝብ መኖሪያ ሆና ነበር ያገኟት፡፡ አሳሾቹ ምስራቅ እስያን ለመድረስ አስበው በድንገት አሜሪካን ስለረግጡ ለነባሩ ነዋሪዎች “ህንዶች /Indians/” የሚለውን ስያሜ አውጥተውላቸው የነበረ ሲሆን በኋላ ደግሞ አሜሪካን በኃይል በቁጥጥራቸው ስር ያደረጉት የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች “ቀይ ህንዶች /Red Indians/” ብለው ጠሯቸው፡፡ የእንግሊዝ ወራሪዎች የዛሬዋን ዩ.ኤስ.ኤ(U.S.A) በቅኝ ግዛትነት በያዙባቸው ዓመታት መሬትን የመሬት ባለቤት ከሆነው ነባር ህዝብ ነጥቀው በቦታው የራሳቸውን ዜጎች ከመተካት አልፈው የነባሩን ህዝብ ማንነት በማጥፋት የራሳቸውን ቋንቋና ባህል ተክለዋል፡፡ በዚህ ሂደት አሁን ባለው ሁኔታ የነባሮቹ አሜሪካውያን (“ቀይ ህንዶች /Red Indians/”) ማንነትና ህልውና በመጥፋት አደጋ ውስጥ ከወደቁት ውስጥ ቀዳሚና አንዱ ሆኗል፡፡
የአውሮፓውያኑ የዘር ማጥፋት ተግባር በዩ.ኤስ.ኤ (U.S.A) ብቻ የተገደበ አልነበረም፡፡ ወራሪዎች (በዋናነትም ስፔይን፣ ፖርቩጋል፣ ብሪታኒያና ፈረንሳይ) በዛሬዎቹ ብራዚል፣ ሜክሲኮ፣ ፔሩ፣ ቺል፣ ካናዳና በሌሎች የሰሜንና የላቲን አሜሪካ አካባቢዎች የነበሩ ህዝቦች ማንነትና ህልውና እንዲጠፋና እንዲመናመን አድርገዋል፡፡ በመሠረቱ በመላው አሜሪካ የነባሩ ህዝብ ማንነትና ህልውና እንዲጠፋና እንዲመናመን የተደረገው በጦርነት ብቻ ሳይሆን ከተሞችንና ሰፋፊ የገበያ እርሻዎችን (Lasrge scale commercial farming) በማስፋፋት ጭምር ነበር፡፡

አፍሪካውያንም የአውሮፓውያኑ ቅኝ ገዥዎች ተፅዕኖ ገፈት ቀማሾች ነን፡፡ በዚህም ለዓለም ህብረተሰብ ተጨማሪ ውቤት፣ ዕሴትና ሀብት መጨመር የሚችሉ ማንነቶችና ቋንቋዎች ጠፍተው (ህልውናችንን ለማጥፋት አውሮፓውያን ያደረጉት መጠነ ሰፊና ዓይነተ-ብዙ ስልቶች በህዝቦች ተጋድሎ በተፈለገው ደረጃ ባይሳካም) በአብዛኛው የአህጉሪቱ ክፍሎች በአውሮፓውያን ማንነት የበላይነት ስር ወድቋል፡፡
ከአውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች ባልተናነሰ መልኩ የአቢሲኒያ ገዥዎች በሀገር አንድነት ስም (ታላቋን ኢትዮጵያ ለመመስረት በሚል) የኩሽቲክና የኦሞቲክ ማንነቶችን አጥፍተው የራሳቸውን ማንነት ለማስፋፋት በርካታ ስልቶችን ተጠቅመዋል፡፡ ቀደምት የአቢሲኒያ ገዥዎች በዋናነት ጦርነትን፣ ጭሰኛ ማድረግንና ማንነትን የማዋረድ ስልቶችን የተጠቀሙ ሲሆን አሁን በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ-አማራ መንግስት ደግሞ የተለያዩ የመሬት አዋጆችንና ፖሊሲዎችን በማውጣት የመሬት ባለቤትነትን የመቀየር አካሄድ /shifting land ownership) እየተጠቀመ ነው፡፡ ሁሉም የመሬት ወረራ ስልቶች በህዝብ ማንነት ላይ ያመጡትንና በማምጣት ላይ ያሉትን ተፅዕኖ ቀጥለን እናያለን፡፡

የአብቹና የገላን ኦሮሞ መጥፋት
ምኒሊክ ፊንፊኔን (በኋላ ስም ቀይሮ አዲስ አበባ ብሎ የጠራውን አካባቢ) በተቆጣጠረበት ወቅት በአካባቢው ይኖሩ የነበሩት የአብቹና የገላን ጎሳዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የኦሮሞ ብሔር አባላት በምኒሊክ ዘመን በተካሄደባቸው የቅኝ ግዛት ጦርነት ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ የደረሰባቸው ከመሆኑም በላይ ከመሬታቸው ላይ በግፍ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ በዚህም የጎሳዎቹ አባላት ቁጥር እጅጉን ተመናምኗል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ያሉት ጥቂት የጎሳዎቹ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት ምክንያት ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተበታተኑ ሲሆን በጣት የሚቆጠሩት ደግሞ በአዲስ አበባ ውስጥ በዘብኝነትና በቤት ሠራተኛነት ያገለግላሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲት የአንትሮፖሎጅ መምህር የሆኑት ዶ/ር ገመቺስ ስለነዚህ የኦሮሞ ጎሳዎች ባጠኑት ጥናታቸዉ ውስጥ እንዳረጋገጡት (ገጽ 102) የጎሳዎቹ አባላት ባለፉት 100 ዓመታት በመሬታቸዉ ላይ በተደረገዉ ፊውዳላዊና ዘመናዊ የግዛት ማስፋፋት (Neo-imperialism) ምክንያት ማንነታቸዉን አጥተዉ፣ ተደባልቀዉና ተበትነዉ ጠፍተዋል፡፡ ምሁሩ በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ከ22 ዓመታት በፊት 150 የሚሆኑ የገላንና የአቢቹ ጎሳዎች አባላት በለቡ፣ በጆሞና በአቃቂ አካባቢዎች የነበሩ ሲሆን በአሁን ጊዜ እነዚህም መሬታቸዉ ተነጥቆ ከምድረ ገጽ ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል፡፡ በተጨማሪም ጥቂት ወንዶችና ሴቶች በተለያዩ የግል መኖሪያ ቤቶችና ሆቴሎች በጥበቃና በቤት ሠራተኛነት ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆን የዘር ግንዳቸዉ ቋንቋ የሆነዉን አፋን ኦሮሞን ከተናገሩ ከሥራ ስለሚባረሩ ቋንቋውን እንደማይጠቀሙና ዘራቸውን ወደ አማራነት ቀይረው እንደሚኖሩ ምሁሩ በጥናታቸው አመላክተዋል፡፡
ከዚህ የጥናት ውጤት በመነሳት ወያኔ/ኢህአዴግ የአርሶ አደር ፓርት ነዉ ወይ? የመሬት ፖሊሲዉስ አርሶ አደሩን መሰረት ያደረገ ነውን? መሬት አይሸጥም አይለወጥም በማለት በህገ-መንግስቱ ውስጥ የደነገገው ለማነዉ? ኢህአዴግ የአርሶ አደሩ ድርጅት ከሆነ መሬትን ለምን የትግሬ ነጋዴዎችና ጥገኛ የድርጅቱ አባላት ስቀራመቱ ዝም ብሎ ይመለከታል? በዘመናዊ የመሬት ወረራ ሂደት ለምን የኦሮሚያና የሲዳማ መሬት ዋነኛ ኢላማ ሆኑ? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሱ አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ ይኸውም በዕድገትና ልማት ስም አቢሲኒያውያን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥንካሬያቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ከማሸጋገር ባለፈ አካባቢዎችን በመቆጣጠር በሌሎች ላይ የበላይነትን ለመቀዳጀትና በማንነትና በአስተሳሰብ የተዋሀደ ህዝብ በኢትዮጵያ እንዲፈጠር ስትራቴጂካዊ ዕቅድ አዘጋጅተው እየተገበሩ መሆኑ ነው፡፡ በራሴ በኩል የአብቹና የገላን ጎሳዎች መጥፋታቸውን የሚያመለክት የጥናት ዉጤት ካነበብኩ በኋላ ራሴን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ባህር ያጠመኩበትን ቀን በመርገምና የጠጣሁትን ጽዋ በማስታወክ ከጨፍጫፍዎችና ከዘራፊዎች ቡድን የወጣሁ ሲሆን ምንም እንኳ አምባገነን ቢሆንም የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ያረጋገጠውን ደርግ ማመስገን እንደሚገባም አመንኩ፡፡
አሳዛኙ ጉዳይ የፊንፊኔ ኦሮሞ የሆኑት አብቹና ገላን ዝሪያ መጥፋት ብቻ አይደለም፡፡ አንጀታችንን የሚያሳርረው ሌለኛው መጥፎ ታሪክ አዲስ አበባ በኦሮሞ ምድር ላይ የተመሠረተና የዚህን ብሔር ማንነት እየበላ የተስፋፋ (አሁንም እየተስፋፋ ያለ) ከተማ ቢሆንም ወደ 4 ሚሊዮን ከሚገመተው የከተማው ህዝብ ውስጥ የኦሮሞ ቁጥር ከ10% የማይበልጥ መሆኑ ነው፡፡ ሌላኛው ጉዳይ ደግሞ አዲስ አበባን ለማስፋፋት እየተደረገ ያለው ስትራቴጂካዊ አካሄድ ዋና ግብ ከተማውን በሰሜን በኩል ከደብር ብርሀን ከተማ (ሸዋ አማራ)፣ በደቡባዊ ምዕራብ ደግሞ ከጉራጌ ጋር በማገናኘት ታላቅ ከተማ /Metropolis/ መፍጠርና ኦሮሚያን ለሁለት መሰንጠቅ ነው፡፡ ይህም የኦሮሞን ህዝብ የነፃነት ጥያቄ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማስቆም ታላቋና የተረጋጋች የአቢሲኒያ ሀገር በኦሮሞ ህዝብ መቃብር ላይ እንትመሰረት ለማድረግ የታለመ ስትራቴጂ ነው፡፡ በርግጥ የኦሮሞ ህዝብ አሁን ዘመኑ የደረሰበትን ስልጣኔ እየተጠቀመ ቀርቶ ጥንት በባህላዊ የአስተዳደር ሥርዓት ውስጥ በነበረበት ዘወቅትም በዘመናዊ መሳሪያ ተደግፎ ማንነቱን ለማጥፋት የተካሄደበትን ዘመቻ በታላቅ ተጋድሎ በማክሸፍ እስከዛሬ አቆይቷል፡፡ የዚህ ትውልድ ትልቁ ኃላፊነትም ይህንን ተጋድሎ መድገም ብቻ ሳይሆን ከአቢሲኒያ ቅኝ ግዛት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነፃ ለመውጣት የሚያስችል ስትራቴጂ በመንደፍና በመተግበር የሰይጣኖቹን የዘር ማጥፋት ተልዕኮ መቅበር ነው፡፡
የሲዳማ ሀዌላ ጎሳ አደጋ ውስጥ መውደቅ
የሐዌላ ጎሳ ከሲዳማ ብሔር ጎሳዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ጎሳዉም እንደ ሌሎች ጎሳዎች ሁሉ በሲዳማ ክልል ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖር ቢሆንም በቁጥር በዛ ብሎ የሚገኘዉ ግን በሀዋሳ ዙሪያ ነዉ፡፡ በርግጥ በሐዋሳ አካባቢ ሌሎች የሲዳማ ጎሳዎችም /ቄዌና፣ ማልጋ፣ አላዋ፤ ጋርቢቾ-ሆሎ፣ የመሬሮ፣ ሀዲቾ፣ አላታ፣ ፋርዳኖ፣ ሳዎላ፣ ጉጄ(ጌርጌዳ - ጋሬ ጋዳ ወይም በጋዳ ሥርዓት የሚመራ ህዝብ)/ ...ወዘተ በብዛት የሚገኙ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሲዳማ ህዝብ እምነትና አገላለጽ የሐዋሳ አካባቢ መሬት ባለቤት የሀዌላ ጎሳ በመሆኑ ሌሎቹ ጎሳዎች በአጠቃላይ ሀዌላ ተብለዉ "ጣላታ" ሆነዉ ይኖራሉ፡፡
ወደ ቁም ነገሩ ስንመለስ የሀዌላ ጎሳም ከላይ ከተጠቀሱት የኦሮሞና የአጌው ብሔሮች ባልተናነሰ ደረጃ የመሬት ወረራው ሰለባ ነው፡፡ ወያኔ ከሀዋሳ ከተማ ሲዳማን በማፈናቀል መሬቱን ለመቀራመት ለሀጩን አንጠባጥቦ ዕቅድ መንደፍ የጀመረው ገና በትረ-ስልጣኑን እንደጨበጠ መሆኑን በዚያን ወቅት የነበሩ የሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት-ሲህዲድ (የአሁኑ ደኢህዴን)ና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) አባላት ያስረዳሉ፡፡ በወቅቱ የደቡብ ክልልን በሞግዚትነት እንዲቆጣጠር የተሾመው አቶ ቢተዉ በላይ በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ከነበረው ከአቶ መለስ ዜናዊና ጠቅላይ ሚኒስትር ከነበረው ከአቶ ታምራት ላይኔ ትእዛዝ በመቀበል ለሲዳማው ተላላኪ ለአቶ ዘርሁን ቃምሶ አጀንዳ ሰጥቶ ሲዳማን ከመሬቱ ለማፈናቀል አቅድ አውጥቶ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ሊታወቅ ችሏል፡፡ በወቅቱ በአርባምንጭ ከተማ በተደረገዉ ስብሰባ አቶ ብተዉ በላይ ያቀረበዉን የሊዝ አዋጅ የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ በነበሩትና ለብሔሩ በሚቆረቆሩት በአቶ ዋቃዮ ዳማሳ አማካይነት ከሸፈ እንጂ ጉዳዩ የተጠነሰሰው የዚያን ጊዜ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት የደቡብ ክልል ፕሬዝደንት የነበሩት አቶ አባተ ኪሾ በጉዳዩ ላይ ብዙ ገፍቶ ሄዶ ብተዉ በላይን ባይሟገትም እንደ ተላላኪው አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ ግን ለህዝባቸው መብት የሚታገሉትን የሲዳማ ልጆች የማሸማቀቅና የሲዳማን ማንነትና ብሄርተኝነት የመድፈቅ ስራ አልሰራም፡፡
ወያኔ በሲዳማ ህዝብ ላይ ያለውን ጥላቻ በግልጽ ያንፀባረቀው የሲዳማ ዞን አስተዳደር ከሐዋሳ መውጣት አለበት ብሎ በተናገረበት ወቅት ነው፡፡ ይህ የሆነው በ1994 ዓ.ም ሲሆን በወቅቱ የጉዳዩ ዋነኛ ተዋንያን የነበሩት ከክልል የቀድሞዉ የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት (የአሁኑ “Puppet” የወያኔ ጉዳይ አስፈፃሚ ጠቅላይ ሚኒስቴር) አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የአቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ የነበረዉ አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ፣ በወቅቱ ምክትል ፕሬዝደንት የነበረው አቶ መለሰ ማሪሞ፡ አቶ መኩሪያ ሀይሌ እና አቶ ፀጋዬ ማሞ፣ ከሲዳማ ዞን ደግሞ አቶ ጋላልቻ ጃንጄና አቶ ጴጥሮስ ወ/ሰንብት ሲሆኑ እነዚህ ከወያኔዉ አምባገነን ከአቶ መለስ ዜናዊ የተቀበሉትን የቤት ስራ ወደ ተግባር ለመቀየር አዋጅ በማዉጣት ያካሄዱትን ሙከራ ጀግናዉ የሲዳማ ህዝብ ታግሎ ዳግም ያከሸፈባቸው ሲሆን በወቅቱ በህዝቡ ላይ በተፈፀመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከ60 በላይ የሚሆኑ የሲዳማ ወጣቶች፣ ህፃናትና ሽማግሌዎች የህይወት ዋጋ፣ ከ200 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እና ከ850 በላይ የሚሆኑ ተወላጆች ደግሞ ያለፍርድ ከቀበሌ እስከ ፌዴራል ድረስ ታስረው ስቃይ ደርሶባቸዋል፡፡ እነዚህን ለህዝብ ማንነትና ጥቅም ብለው መስዋዕትነት የከፈሉትን ወገኖቻችንን የታሪክ ጀግኖች ብለን እንጠራቸዋለን፣ ሁሌም እንዘምራላቸዋለን፡፡
በተመሳሳይ ወያኔ የሲዳማን መሬት ለመቆጣጠር ሌላ ዕቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ እንደሚገባ በማመኑ በ2004 ዓ.ም የሜትሮፖሊታን (የትላልቅ ከተሞች ምስረታ) ዕቅድ በአቶ መለስ ዜናዊ አማካይነት ተዘጋጅቶ ይፋ ተደረገ፡፡ በዚህ ወቅት ወያኔና ተላላኪዎቹ ያለ የሌለ ኃይላቸውን ተጠቅመው የሀዋሳን መሬት ለመዉረር ከፍተኛ ዝግጅት ያደረጉበት ወቅት ነበር፡፡ ይህንን ዕቅድ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የራሱን ሀሳብ በመጨመርና በሲዳማ ህዝብ ላይ ያለዉን ጥላቻ በማንፀባረቅ ሰፋ አድርጎ ጽሁፉን ከፃፈው በኋላ ተልዕኮዉን እንዲያስፈጽም ለአቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ ትዕዛዝ ሰጥታል (በመሠረቱ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ አቶ ሽፈራዉን በኮራፕሽን እንደሚጠረጥረዉና እንደማይወደዉ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ሲዳማ እንደ ቡና ሲፈላ የሚኮረኩምለት ሰው ነው ብሎ ስለሚያምን ብቻ አብረው እንደሚሰሩ እራሱ ኃ/ማርያም ከተናገረው ምስጢራዊ ንግግር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህም አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ ለራሱ መኖር ከፈለገ የሲዳማ ብሔር ማንነት እንዲጠፋ የሚታቀደውን ዕቅድ ጭምር ወደኋላ ሳይል እንዲመራ ግዴታ የተጣለበት ሰው መሆኑን ያመለክታል)፡፡
የወያኔ መንግስት የሲዳማን ህዝብ አፈናቅሎ የሐዋሳን መሬት ለመቆጣጠር የተለያዩ ስልቶችንና ዕቅዶችን በመቀየስ ተንቃሳቅሷል፡፡ ዕቅዶቹንና ስልቶቹን ወደ ተግባር ለመቀየርም የሲዳማ ተወላጆች ነን የሚሉ ሆዳሞችንና የሌሎች ብሔረሰቦች ተወላጆችን በተላላኪነት እንደሚጠቀም አይተናል፡፡ እነዚህን የግፍ ተግባር የመሩትን የሲዳማም ሆነ የሌሎች ብሔሮች ተወላጆችን ታሪክ ይፋረድባቸዋል፤ ህዝባችንም የሚገባቸውን ዋጋ ይከፍላቸዋል፡፡ በተለይም በአቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝና አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ግንባር ቀደም መሪነት በወቅቱ የሀዋሳ ከተማ የሽግግር አስተዳደር ከንቲባ የነበረው የሲዳማው ተወላጅ ሟቹ አቶ ለገሰ ወልዴ፣ የከተማ አስተዳደሩን ኢኮኖሚና ገቢ ሲመራ የነበረው የወላይታው ተወላጅ አቶ ገ/መስቀል ጫላ፣ የማዘጋጃ አገልግሎቱን ይዞ የነበረው የካንባታው ተወላጅ አቶ ሚካኤል ጦቢያስ፤ የመሬት አስተዳደሩን ሲያተራምስ የነበረው የጉራጌው ተወላጅ አቶ መለሰ ሚዴቅሳ/የአቶ መኩሪያ ኃይሌ ዘመድ/ የሰሩት ስራ የሚረሳ አይደለም፡፡ እነዚህ የወያላ ባህሪይ ያላቸው ሰዎች የሲዳማን መሬት ለወያኔ ወገኖች ከማከፋፈላቸውም በላይ ለራሳቸው ብሔርም በሐዋሳ መንደር መስርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የጉራጌና የካንባታ መንደር በአዲሱ ስታዲዬም አካባቢ መኖሪያ ፎቆች ተገንብተውለት የተመሠረተ ሲሆን የወላይታ መንደር ደግሞ በአሮጌ ገበያ፣ በውቁሮና በኮረም አካባቢዎች የሚገኙ የቀበሌ ቤቶችን ወላይታዎች በብዛት እንዲይዙ ተደርጎ ተጠናክሯል፡፡ በሌሎች የሐዋሳ ቀበሌዎችም ቢሆን አብዛኛው ነዋሪ ሲዳማ ሳይሆን መጤው ህዝብ ነው፡፡ በዚህም ድሆቹ የሲዳማ ተወላጆች ለባለፎቆቹ ቱጃሮች (የግፍ ሀብት ላከማቹት) ዘበኛ ሆነዋል፡፡ ጥቂት የሲዳማ ልጆች ቢኖሩ እንኳን ሐዋሳ ላይ መሬት ያገኙት በአቶ አያኖ በራሶ የሚመራው የከንቲባ ኮሚቴ የሲዳማን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባደረገው ሙከራ ነበር፡፡ ይህ ከንቲባ ኮሚቴ እስከ አሁን ድረስ ከተዋቀረዉ የከንቲባ ኮሚቴ የተሻለ ጥቅም ለሲዳማ ህዝብ አስገኝቷል ብሎ መናገር ይቻላል፡፡
ወያኔ የሲዳማ ብሔር ማንነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደረገው በየጊዜው እየቀያየረ በሚያወጣቸው የከተማ ልማት ፖሊሲዎች መሬት በመንጠቅ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንስ የሲዳማ ህዝብ መልከ-ብዙ ከሆኑና ምንም ዓይነት ባህላዊ ወይም ሥነ-ልቦናዊ ግንኙነት ከሌላቸው ብሔረሰቦች ጋር አንድ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ በጠመንጃ ኃይል በማስገደድ ጭምር ነው፡፡ ህዝባችን ደግሞ ይህ አደረጃጀት የሚያመጣበትን እርግማን ገና ከጧቱ ስለተገነዘበ ትግል ከማካሄድ ወደ ኋላ ብሎ አያውቅም (ምንም እንኳን ወያኔ የህዝብን ድምፅ የሚሰማ ጆሮ የተደፈነበት ቡድን በመሆኑ ለጥያቄው ምላሽ ባይሰጥም)፡፡ ለአብነትም በሥርዓቱ ላይ ያለውን ተቃውሞ በምርጫ 97 ወቅት ካርድ በመከልከል ከመግለጹም በላይ ወያኔ የህዝቡን ድምፅ በመንጠቅ የሰራውን አሳፋሪ ስራ በተቃወመበት ወቅት የልጆቹን ህይወት በወያኔ ጥይት አጥቷል፡፡ ከዚህ በኋላም ህዝቡ ጥያቄውን ሳያቆም በመቀጠል በህገ-መንግስት ተብዬዉ ህገ-ወያኔ አንቀጽ 42 ላይ የተቀመጠዉን ድንጋጌ ተከትሎ ሪፌረንዴም እንዲደረግ ሀምሌ 5/1997 ዓ.ም በአቶ መለሰ ማሪሞና ገረሙ ጋርጄ መሪነት የዞኑ ምክር ቤት ጥያቄዉን አጽድቆ ጉዳዩ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ለህግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ እንዲመራ አድርጎ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የወያኔዉ ተንኮል-ቀማሪ /Evil-Strategist/ አቶ መለስ ዜናዊ ክፉኛ የተደናገጠ ሲሆን የድንጋጤውም ዋና መነሻ ከምርጫ ጋር በተያያዘ አገርቷ በብጥብጥ ዉስጥ ስለነበረች ይህንን ጥያቄ ልክ አይደለም ብሎ ውሳኔ መስጠት በአካባቢዉ ፍተኛ ነውጥ እንደሚፈጥርና በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚሆንበት በማሰብ ነበር፡፡ ይሁንና በመሰሪው አቶ መለስ ዜናዊ ፊታዉራርነትና በአቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ ተላላኪነት ህግ ከሚፈቅደዉ ዉጭ የሲዳማ የክልል ጥያቄ ተቀልብሷል (ስለ እዉነቱ ከሆኔ ጥያቄዉን የተቃወመዉ ብቸኛዉ ሰዉ አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ ነዉ)፡፡ በነገራችን ላይ አቶ መለስ ዜናዊ ጥያቄውን ለማኮላሸት ባቀደበት ወቅት በነሀሴና በመስከረም ወራት ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በተደረገው ዉይይት ላይ አቶ በረከት ስምኦን እንዲገኝ በማድረግ የሲዳማ የክልል ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለዉና 44 ድንኳን አንጥልላችሁም በማለት (በጎንደር ታቦት ማስመሰሉ ይሁን ምን ለማለት ፈልጎ እንደሆነ አይታወቅም) ያልተገባ ንግግር አድርጎ ነበር፡፡ በወቅቱ አቶ በረከት አፉን ሞልቶ ሲናገር የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ አላቀረበም፤ ይልቁንስ የክልል ጥያቄ አለን ብለው አካባቢውን የሚበጠብጡት ጠባቦችና የኪራይ-ሰብሳቢነት አባዜ የተጠናወታቸው ቡድኖች ናቸው ብሎ ነበር (መቼ ጥናት ወይም ሪፌረንደም ተደርጎ ጥያቄው የሲዳማ ህዝብ አለመሆኑ ተረጋገጠ ለምለው ሳይንሳዊ መከራከሪያ ወያኔ መልስ የለውም)፡፡
በዚህ ንግግሩ የሲዳማ ተማሪዎች የምን ጊዜም አጋሩ ከሆኑት የኦሮሞ ልጆች ጋር በመቀናጀት የሲዳማን ህዝብ መሳለቁንና ለብቻቸዉ እንዲያናግራቸዉ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በሲዳማ ባህል አዳራሽ ስብሰባ ተደረገ፡፡ በዚህን ወቅት ተማሪዎቹ የሀይል እርምጃ እንደሚወስዱበት ሲገልጹ አቶ በረከት እኔ በረሃ ብዙ ጊዜ ተዋግቻለሁ ይሁንና እንደዛሬ ፈርቼ አላዉቅም በማለት ፍርሀቱን ከገለፀ በኋላ ከአዳራሹ በህይወት ለመዉጣት ፈልጎ ጠይቅ ያላችሁኝን ይቅርታ ጠይቄያለሁ ብሎ እስከመናገር ተገዶ ነበር፡፡ ነገር ግን ሰውዬው በሲዳማ ሕዝብ ላይ በነበረዉ ቂም ላይ ይህንን ጨምሮ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር በጉዳዩ ላይ በጥልቀት በመምከር አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ ዋና ተዋናይ ሆኖ ከወረዳ እስከ ምኒሊክ ቤተ መንግስት ድረስ ለሆድ የሚገዙትን የሲዳማ ልጆች እንዲመለምል አድርጎ የሲዳማን ሕዝብ ከ100 ዓመታት በፊት ጀምሮ ሲታገል የኖረውን ጥያቄ አኮላሽቷል፡፡
የወያኔ መሰሪ አቶ መለስ ዜናዊ የህዝቡን ጥያቄ ለማኮላሸት ያቀረባቸው ምክንያቶች ሰውዬው በሌሎች ብሔረሰቦችም ላይ ምን ያህል ጥላቻ እንዳለበት በግልጽ የሚያሳዩ ነበሩ፡፡ በወቅቱ የሲዳማን ሽማግሌዎችና ወጣቶች ሰብስቦ ሲናገር ጥያቄዉ ለእናንተም ሆነ ለኢህአደግ አይጠቅምም፤ ሲዳማ ክልል ሆኖ ከወጣ ጠባብ ገበያና የተፈጥሮ ሀብት ይዞ ስለሚቀር ሐዋሳም ሆነ መላው ሲዳማ ይቀጭጫል፤ ኢህአዴግ ደግሞ በደቡብ ክልል የሚተማመነው ሲዳማን ብቻ መሆኑንና ሌሎች ብሄሮች በክልሉ ያለዉን የጥገኛ ካምፕ ለማጥቃት እምነት የማይጣልባቸው ከመሆናቸውም በላይ አቅመ-ቢስ እንደሆኑ በመግለፅ፣ ሲዳማ ክልል ሆኖ ሲወጣ ለብቻው የሚደራጀው አዲሱ የደቡብ ክልል ከአዲስ አበባ ዉጭ የሚፈጠር ሌላኛው የቅንጅት ክልል እንደሚሆን በመተንተን፣ እንደ ጉራጌ፣ ሀዲያ፣ ካምባታ፣ ጋሞና ጎፋ ያሉ ብሔሮች/ብሔረሰቦች ጥገኛና የአማራ አሽከሮች ናቸዉ ብሎ በመፈረጅና ወላይታም ቢሆን ድሀና በየቦታው ለቃቅሞ ስለሚኖር ወኔ የሌለውምና ከአማራ እጅ ማምለጥ አይችልም ብሎ ከተናገረ በኋላ ሲያጠቃልል እነዚህን የጥገኛ አቀንቃኞች የሚናኮላሸዉ የደቡብን ካምፕ በሲዳማ የበላይነት እንዲመራ በማድረግ ነው ብሎ እንባዉን እየቀያየረ ደግሞ ደጋግሞ አስረዳ፡፡ ይህንን ብቻ ሳይሆን ጫማ ከጠበበ ጫማዉ ይቀየራል እንጂ እግር አይቆረጥም በማለት (ኃ/ማሪያም እኛን ለመምራት ብቁ አይደለም ካላችሁ እቀይረዋለሁ፤ ሀዋሳ ከተማም ብትሆን ለናንተዉ ነው የሚታድገው የማስተዳዳሩ ሥልጣንም በራሳችሁ እጅ ነው፤ ደቡብ ዩኒቨርሲቲ የነበረዉን ሀዋሳ ዩኒቨርሲት ተብሎ ይቀየራል፤ የአለታወንዶ-ቤንሳ ዳዬ መንገድ ይሰራል (በ10 ዓመታት በኋላ ያለቀው መንገድ)፤ በአጠቃላይ የሚያስልጋችሁ ልማት እንጂ ክልል ብቻውን ምን ይጠቅማል በማለት የማጭበርበር ድስኩሩን ጨርሶ ቢሄድም ህዝቡ ግን ምንም አልተቀበለውም ነበር፡፡ እኛ ተቀበልንም አልተቀበልንም ውጤቱ አቶ መለስ የሚፈልገው ዓይነት ሆኖ የሲዳማ ህዝብ በምኒሊክ ቅኝ አገዛዝ የተነጠቀውን መብት በዳግማዊ ሚኒሊክ በአቶ መለስ ዜናዊ ዘመንም ዳግም እንደተነጠቀ ለመቆየት ተገዷል፡፡ በዚህም ምክንያት የወያኔ ተላላኪ የሆኑት አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ፤ አለማዬሁ አሰፋ፤ መኩሪያ ኃይሌ፣ ተስፋዬ ቤልጅጌ፣ መለሰ አለሙ፣ ፀጋዬ ማሞና ደነቀ ማሞ (የፀጋዬ ማሞ ወንድም) የሀዋሳ መሬት የሲዳማ ሳይሆን የሁላችንም ነዉ የሚል አመለካከት ከማራመድ አልፈው አስፈላጊ ከሆነ ሐዋሳ የፌዴራል ትሆናለች፣ ሲዳማ ደግሞ የዞኑን ማዕከል ይቀይራል እንጂ እኛ የምንወጣበት ጊዜ አልፏል ብለው በተለያዩ መድረኮች እስከመናገር ደርሰዋል፡፡
ወያኔ ሲዳማን እንዳጭበረበረ በግልጽ የታወቀው የአዋሳ ከተማ የድሮ ስሟ ሐዋሳ ስለሆነ ከዛሬ ጀምሮ ሐዋሳ ተብሎ ይጠራል በማለት የማንነት ጥያቄያችንን ”አ“ ፊደልን በ ”ሀ“ ፊደል የመተካት ያህል አውርዶ በተመለከተበት ጊዜ ነበር /አንዳንድ ምሁራን በከንፈር አገልግሎት (Leap service) አታለለ ብለዉ ይቀልዳሉ/፡፡ እኛ የከተሞች ስም ይቀየርልን ብለን ጠይቀን አናውቅም፡፡
ጥያቄያችን ይህ ቢሆን ኖሮ ማንንም ሳንጠይቅ በክልላችን ውስጥ ያሉትን ከተሞች ስማቸውን መቀየር እንችል ነበር /ለምሳሌ ይርጋዓለም፣ ኬላ፣ ወዘተ…./፡፡ ይህ የፊደል ጨዋታ ያልተዋጠላቸው የሲዳማ ሽማግሌዎች ለመሰሪው አቶ መለስ ዜናዊ በሲዳማ ዘንድ ትልቅ አክብሮት ያለውንና የእዉኔት ተምሳሌት የሆኔዉን ሴማ /ቡሉኮ/ ከሰጡት በኋላ “ተቸግረያለሁና ለጊዜዉ ጥያቄዉን አቆዩልኝ ስላልክ አቆይተንልሀል:: ነገር ግን ጥያቄያችን የማንነት ጥያቄ እንደ መሆኑ መጠን ምላሽ እንፈልጋለን፡፡ እንቢ ብለህ ለጥያቄያችን ትክክለኛ ምላሽ የማትሰጥ ከሆኔ ይህ የእዉኔት ምሳሌ የሆነው ሴማ /ቡሉኮ/ ይፈርድብሃል” ብለው ከአዳራሹ ሸኙት፡፡
እዉነትም ሴማ ይፈርዳል!! ሰውዬው አዕምሮው እየበሰለ የመጣ ይመስላል፣ ስለዚህ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ሳይጠቅም አይቀርም ተብሎ በተጠበቀበት ወቅት ከነድብቅ ሴራዎቹ በድንገት መቃብር ወረደ (በርግጥም ለእሱ የሚገባው ቅጣት ነው፤ ፈጣሪያችንም ህዝብ በንፁህ ልቦና ውስጥ ሆኖ የሚያቀርበውን ማመልከቻ ተቀብሎ በቅንነት የሚፈርድ አምላክ ነው)፡፡ ምን ይህ ብቻ! የሲዳማ ህዝብ በጉዱማሌ ማዕከል የጫንባላላ በዓል ለማክበር በወጣበት ወቅት አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤን ከዚህ በኋላ ወደ እኛ አይመልስህ ብሎ ተናገሮ በአስረኛዉ ቀን ከሥልጣኑ ተነቅሎ የለም እንዴ!! ለሲዳማ እዉነት እስጎሆይ!! (Hoola sidaamu halaalira!!) አቶ ሽፈራው በጉዳማሌ የተረገመውን እርግማን በአለታ ወንዶ ከተማ ሽማግሌዎችን ሰብስቦ በማታለል እርግማኑን እንዲፈትሉት ቢጠይቅም የህዝቡ ጥያቄ ሳይመለስ የጉዳማሌ እርግማን በአዳራሽ ውስጥ እንደማይፈታ መገንዘብ ይገባዋል!
የሲዳማን የክልል ጥያቄ በአግባቡ መመለሱን ትቶ የወያኔ ቡድን ተላላኪዎቹን ከኋላ አሰልፎ የህዝባችንን መሬት ለመቀራመት እንዲመቸው አንድ ያልተጠበቀ እርምጃ ወሰደ፡፡ ይኸውም በ1999 ዓ.ም የወረዳ አደረጃጀት በአዲስ መልክ በተዋቀረበት ወቅት የሐዋሳ ዙሪያ ወረዳን በሶስት ወረዳዎች አደራጀ፡፡ አዲሶቹ ወረዳዎችም ዶሬ ባፋኖ፣ ወንዶ ገነትና ማልጋ ተብለው የተሰየሙ ሲሆን ወደ ወንዶ ገነት ወረዳ ከተጠቃለሉ 19 ቀበሌዎች ውስጥ 4ቱ ቀበሌዎች በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ አቀናባሪነትና በጥቂት ሆዳም የጉጂና የማልጋ ሲዳማ ልጆች ተላላኪነት ወደ ኦሮሚያ እንዲካለል አደረጉ (እነዚህ ጭንቅላት የሌላቸው የወያኔ ተላላኪዎች ያላወቁት አንድ እውነታ ግን የሲዳማና የኦሮሞ ህዝቦች ፈጣሪ ወንድም አድርጎ የፈጠራቸው ህዝቦች እንደመሆናቸው መጠን የወንዶ ገነት 4 ቀበሌዎች ቀርቶ መላው ሲዳማና ኦሮሞ አንድ ላይ ቢቀላቀል ለሁለቱም ህዝቦች የጥንካሬ እንጂ የመለያየትና የመድከም ምልክት አለመሆኑን ነው፡፡
የሲዳማ ህዝብ ጀግንነቱን ሲገልጽ ገራርሻ የሚያደርገው በወንደሙ ህዝብ ቋንቋ በአፋን ኦሮሞ አይደለምን!!)፡፡ እዚህ ላይ የሚገርመው ወያኔ የሐዌላ ጎሳ አንድ እራሱን የቻለ ወረዳ መሆን እየቻለ በሐዋሳ ዙሪያ ያሉትን 12 የሀዌላ ገጠራማ ቀበሌዎችን ወደ ከተማ ክልል እንዲገባ በማድረግ በክፍለ-ከተማ ደረጃ ማደራጀቱና ለመሬት ወረራው ሁኔታዎችን ማመቻቸቱ ነው፡፡ ይህም የህዝቡ ማንነት አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ በር ከፍቷል፡፡
ከዚህ በኋላ በሀዋሳ የመሬት ወረራው ተጧጧፈ፡፡ ለአብነትም ከ1999 ዓ.ም በፊት በዳቶ ቀቤሌ በጥቂቱ የተጀመረው መሬት የመውረር ተግባር ከ1999 በኋላ ነጋዴ መሰል ደላላዎችና ከመንግስት አመራሮች ጋር በመሰባጠር ምንም ለማያዉቀዉ አርሶ አደር የማይጠቅም ገንዘብ (ከ2500 ብር በታች) በመስጠት አርሶ አደሩን በፍጥነት እያፈናቀሉ መሄድ ጀመሩ፡፡ በጊዜ ሂደት የመሬት ወረራው እጅጉን ተፋፍሞ ስለነበረ የመሬት ዋጋውም የተወሰነ መሻሻል እያሳየ ሄደ፡፡ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ሲታስረዳ ከቀበሌው መሬት የገዛችው አንዲት ሴት በአንድ አጋጣሚ ያለችዉን ላዉጋችሁና 2000 ካሬ ሜትሩን በ40000 ብር የገዛችዉ ሲሆን እንዴት ደፍረሽ ይሄንን ሁሉ ገንዘብ አወጣሽ ተብላ ሲትጠየቅ አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ 2000 ካ.ሜ ላይ ከብት እያረባ ነው ስለተባለ ምንም አልሆንም ብዬ ነዉ የደፈርኩት ብላ የተናገረች ነገር ወረራዉን ያበረታታዉ አመራሩ መሆኑን በግልፅ ያሳያል፡፡ ወረራዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ አድማሱን እያሰፋና መልኩን እየቀየረ በመሄድ ከ2001 ዓ.ም ወዲህ ወደ ወሜ ጋሻ፣ ሂጣታና ሀላዴ ጊምቢ ገነት የተስፋፋ ሲሆን በዚህ ወቅትም በሲዳማ ዞንና በሌሎች ዞኖች/ልዩ ወረዳዎች ተመድበው የሚሰሩ የደኢህዴን አመራር ተብዬዎቹ ከክልል እስከ ከተማ አስተዳደር ድረስ ከዳላሎች ጋር ሆነው በመሬት ወረራው ሂደት በስፋት ተሳትፈው እንደ ነበር ይታወቃል፡፡
በሐዋሳ (በሀዌላ) አካባቢ የመሬት ወረራው ያስከተለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ለማወቅ አንድ ጥናት እየተካሄደ ሲሆን ለጥናቱ የሚሆነውን መረጃ ለመሰብሰብ የቡድን ዉይይት (Focus group discussion) ሲካሄድ አንድ አርሶ አደር አባት “መሬቱን የሚትሸጡት ከተማ መግባት ፈልጋችሁ ነዉ ወይ?” ተብሎ ለተጠየቀዉ ጥያቄ መልስ ሲሰጡ “እየሸጥን ያለነዉ አንድ ወቅት ላይ አንድ በከተማ ዉስጥ አመራር የሆነ ሰዉ ሰብስቦን መሬቱ የመንግስት ስለሆነ ተነሱ በተባላችሁ ጊዜ ትነሳላችሁና እስከዚያ ድረስ ብቻ ነዉ የሚትጠቀሙት ብሎ ስለን ለካ መሬታችንን ልትቀሙን ነዉ በማለት መቸብቸብ ጀመርን” ብለዋል፡፡ አጥኚው እንደዚህ ያለው አመራር ማን እንደሆነ ሲያጣራ ግርማ ግንቦ የሚባል የሀዋሳ ከተማ የገጠር ፖሎቲካ ዘርፍ ኃላፊ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ አመራር ተግባር በመነሳት እና ሌሎች መረጃዎችን በመመልከት አሁን ያለዉ አመራር ምን ያህል ለወገኑ የማይቆረቆርና የመሀይም ጭንቅላት ባለቤት (Illiterate minded) እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል::
አጥኚው ከአርሶ አደሮቹ ጋር በነበረው ቆይታ ከዚህ በኋላ ከተማ ገብታችሁ እንዴት ትኖራላችሁ? አመጋገቡንስ ታዉቃላችሁ? ብሎ ሲጠይቅ “ልጄ ለእኛ በችግር ወቅት ዋስትናችን የእንሰት ተክል ነበር፣ ቦቆሎም በብዛት እናመርት ነበር፣ መሬታችንም እንደ ወንዶ ገነት መሬት ለም ነዉ፤ የሚንመገበዉም ባህላዊ ምግቦቻችንን ከእርሻችን በመጠቀም ነበር፤ ምስቶቻችንም ቢሆኑ ከሲዳማ ባህላዊ ምግብ ዉጭ ሌላ ምግብ ማዘጋጀት አይችሉም” ብለው ካብራሩ በኋላ “አሁን ግን መሬታችንን ለገዙ ሰዎች ዘበኛ በመሆን ሞታችንን ከመጠባበቅ ባለፈ ምን ተስፋ አለን? የእኔ ሞስት ቀላል ነው ችግሩ ግን የጎሳችን ዘር መጥፋቱና ቋንቋችን የሆነው ሲዳሙ አፎ እንዲሁም አጠቃላይ ማንነታችን መደብዘዙ ነው” ብለዋል፡፡ በእውነቱ ከሆነ ሰብዓዊነት ላለው ለማንኛውም አካል ይህ የአርሶ አደሮች አገላለጽ አንጀት የሚበላ ጉዳይ ነዉ፡፡ ለወያኔና ለተላላኪዎቹ ግን ደንታ አይሰጣቸውም፡፡
በዚህ ዓይነት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ያለው አርሶ አደር ከጥንት ጀምሮ ከከኖሩት ቅድመ-አያቶቹ በወረሰው መሬት ላይ ለሰራው መኖሪያ ቤት 40,000 ብር፣ ለእርሻ መሬቱ ደግሞ በካሬ ሜትር 3500 ብር እንዲከፍል ዕቅድ መውጣቱ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ካልቻለ በከተማው ውስጥ መቆየት እንደማይችልና መሬቱን ለከተማው አስረክቦ እንዲወጣ በደኢህዴን አመራር በኩል (ለዛውም የሲዳማ የገዛ ልጆቹ ጭምር ባሉበት) ተነግሮታል፡፡ ይህም ሌላ አሳዛኝ ኢሰብዓዊ ጉዳይ ሆኖ ሰሞኑን ብቅ ብሏል፡፡
ገና ከጧቱ ለአርሶ አደሩ እቆረቆራለዉ ብሎ በህገ-መንግስት ተብዬው ወረቀት ላይ ጭምር መሬት የመንግስት እንደሆነ የደነገገው የወያኔ/ኢህአደግ ቡድን ተዋናይ አቶ መለስ ዜናዊ በመሬት ላይ ድርጅቱ የያዘውን አቋም ሲያብራራ “መሬት አይሸጥም/አይለወጥም ያልነው ቀደም ብለው ሀብት የያዙ ፊውዳሊስቶችና ነጋዴዎች (አማራ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ...) አርሶ አደሩን በትንሽ ብር እያታለሉ መሬቱን እንዳይቀራመቱ ነዉ” በማለት ሲያብራራ የነበረ ሲሆን ጭቁኑ ሕዝብም በአብዛኛዉ አንቀጹን የተቀበለዉ ይህ ነገር በርግጥም ሊከሰት ይችላል በማለትና መሬቱን ከወረራ ይጠብቅልኛል ብሎ በማሰብ ነበር፡፡ ይሁንና አንቀጹም እያለ “መሬት መሸጥ/መለወጥ በኢህአደግ መቃብር ላይ ነው” ብሎ የተናገረው ሰውም በህይወት እያለ (አሁን ወደ መቃብር ቢወርድም) የሲዳማ ሕዝብ በተለይም የሐዌላ ጎሳ መሬት ተወረረ፡፡ ለካ የህገ-መንግስቱ ድንጋጌ የተዘጋጀው ወያኔ በቂ ካሳ ሳይከፍል አርሶ አደሩን እያፈናቀለ መሬት በቀላሉ መቀራመት እንዲችል እንደሆነ አሁን ግልጽ ሆኗል፡፡ በመሠረቱ አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ኢህአደግ መሀላውን ረስቶ በተለያዩ የመሬት ፖሊሲዎች አማካይነት በህገ-መንግስቱ የተቀመጠውን ድንጋጌ ሸርሽሮ መሬትን ወደ ግል ይዞታነት የሚቀይር አካሄድ (liberalization) መከተል ጀምሯል፡፡ የዚህ ምስጥርም የወያኔ ባለሀብቶች በግፍ ባካበቱት ሀብት ብሊዬነር መሆን በመቻላቸው አሁን የተጠየቁትን ዋጋ በመክፈል የፈለጉትን ያህል መሬት መግዛትና ነባሩን የህዝብ ማንነት አጥፍተው በምትኩ የራሳቸውን አዲስ ግዛት (New Empire) መፍጠር የሚችሉ መሆኑ ነው፡፡
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በዳቶ፣ በአላሙራ፣ በጊምቤ ገነት፣ በሀላዴ፣ በሂጣታ፣ በዱሜ፣ በጫፋ ኮቲጃዌሳ፣ በቱሎና በገመጦ-ጋሌ (ቱላን ጨምሮ) እንሰት ተክለዉ፣ ከብት አርብተዉ፣ ቋንቋቸዉ የሆኔዉን ሲዳሙ አፎ ተናግረዉ፣ በራሳቸዉ ጭሜሳ ተዳድረዉ፣ በጉዱማሌ ክቡር የሆነውን ፍቼ-ጫንባላላ በዓላቸውን አክብረውና ሌሎች እሴቶቻቸውን ጠብቀዉ ይኖሩ የነበሩት የብሔሩ አባላት በተለይም የሀዌላ ጎሳዎች በተካሄደባቸው የመሬት ወረራ ማንነታቸዉን ከማጣታቸውም በላይ ህልውናቸውም አደጋ ውስጥ ወድቋል፡፡ እዚህ ላይ አንድ አሳፋሪ ክስተት ብናነሳ ከከተማ አስተዳደሩ ተመልምለዉ የተወጣጡ የአቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ መዋቅር አካላት በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የአካባቢው ህዝብ ለማወያየት ባዘጋጇቸው መድረኮች ላይ ሙሉ በሙሉ ለማለት በሚያስችል ደረጃ የአማርኛ ቋንቋን መስማትና መናገር የማይችለዉን ሕዝብ በአማርኛ እንዲናገሩ በማስገደድ ከህዝቡ ጋር ምንም ሳይግባቡ የተለያዩባቸው ወቅቶች በርካታ መሆናቸውን ነው፡፡ ይህ የሚያረጋግጠው የወያኔ ተላላኪዎች የሲዳማ ማንነት ከሐዋሳ ከተማ ብቻ ሳይሆን በከተማ አስተዳደሩ ስር ከተጠቃለሉ የገጠር ቀበሌዎች ጭምር እንዲጠፋ ወገባቸውን ታጥቀው እየሰሩ መሆናቸውን ነው፡፡
አዲሱን የወያኔ የከተማ ልማት ፖሊሲዎችን ወደ ተግባር በመቀየር የሐዋሳ ከተማን በህዝብ ማንነት መቃብር ላይ የማስፋፋትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ትልቁ ተልዕኮ የተሰጠው በአሁኑ ወቅት የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ለሆነው ለአቶ አክልሉ አዱላ፣ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ለሆነው ለአቶ ቴዎድሮስ ገቢባ፣ በከተማ አስተዳደሩ የደኢህዴን ጽ/ቤት ኃላፊ ለሆነው ለአቶ ባጢሶ ዌድሶና በእናትዋ ጎጃሜ ለሆነችዉና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ስራ አስክያጅ ለሆነችው ለወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ ሲሆን ተልዕኮዉን ከማስፈጸም አንፃር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሴ ዳልኬ (አሳዛኙ ርዕሰ መስተዳድር) ከፍተኛ ኃላፊነት ተሰጥቶታል (አሳዛኙ ርዕሰ መስተዳድር የተባለበት ምክንያት አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከአሁን በኋላ ስራ ይበዛብኛል በማለት ከዚህ በኋላ ማናቸውንም ተግባር አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ በሚሰጠው አመራር እንዲፈጽም በነገረው መሰረት አቶ ሽፈራዉ በአንገቱ ላይ ገመድ አስገብቶ እየጎተተዉ ያለ ርዕሰ መስተዳድር ስለሆነ ነዉ)፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋልና አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ በሲዳማ ዞንና በሀዋሳ ከተማ ላይ ያለዉ የሥልጣን ጣልቃ ገብነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ከፍተኛ ደረጃ የተሸጋገረ ሲሆን እንዲፈጸምለት የሚፈልጋቸውን አንዳንድ ጉዳዮች ከከንቲባዉና ከሲዳማ ዞን አስተዳዳሪው ጋር በመነጋገር አቶ ደሴ ሳያዉቅ እንደሚያጨርስ ምስጢራዊ መረጃዎች አረጋግጠዋል፡፡ ስለዚህ አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ በአሁኑ ሰአት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ብቻ ሳይሆን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳርር ጭምር ነዉ(አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ አቶ ሽፈራው ይህንን ከፍተኛ ስልጣን እንዲይዝ ያደረገው ከምርጫዉ 2007 በኋላ ሕወሀቶች ለጠቅላይ ሚኒስቴርነት አይመጥንም ብለዉ ልያነሱት ስያሴሩ ቀላዋጩ ሽፈራዉ ሽጉጤ ሰምቶ ስልጣኑን ለራሱ ማግኘት እንደማይችል ካረጋገጠ በኋላ ኃ/ማርያም በጠቅላይ ሚኒስትርነቱ እንዲቀጥል ከቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት አዜብ መስፍንና ከሌሎች የሕወሀት መሪዎች ጋር አስታርቆት ጠቅላይ ሚኒስቴርነቱን እንዲቀጥል በማድረጉ ነው ይባላል)፡፡
በኢንዱስትሪ ልማት ሰበብ የሚካሄድ ሰፈራና መዘዙ
በሐዋሳ ከተማ ኢንዱስትሪ ማቋቋም አስፈላጊ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጥያቄ አንስተን ስንመለከት ከተማዋ የቱሪስት ከተማ እንደመሆንዋ መጠን ገቢዋን እንደ ግብጹ ሸልማርሼክ ወይም አለክሳንድሪያ፣ እንደ ፈረንሳዩ ፓሪስ እድገቱ በቱሪዚም ላይ ብቻ መመስረት ስለሚችል ኢንዱስትሪ አስፈላጊ አይደለም ወደሚለው መደምደሚያ እንደርሳለን፡፡ ታዲያ ለምንድን ነው ወያኔ በሐዋሳ ላይ ቻይና ሰራሽ ቆሻሻ ኢንዱስትሪዎች እንዲገነቡ እያደረገ ያለው?
በአሁኑ ወቅት በሐዋሳ ከተማ በአካባቢዉ አጠራር ዎሳሌ በሚባለዉ ቦታ የኢንዱስትሪ ክልል ታጥሮ ከቻይናውያን ባለሀብቶች ጋር የወያኔ አባላት አክስዮን (Share) ተገዝቶላቸው በርካታ ፋብሪካዎችን መያዝ የሚችሉ ኢንዱሰትሪዎችን እየገነቡ ነው፡፡ ለዚህ የሚሆነውን መሬት ለዶ/ር አርከቤ እቁባይ (ለወያኔ የኢንዱስትሪ ልማት እንዲያመጣ የተሾመ ሰው) ያስረከበው አቶ ብሩ ወልዴ (የቀድሞ የማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ) ነበር፡፡ በመሠረቱ በሀዋሳ ዙሪያ ከሀይቁ ማዶ የሚገኘዉን መሬት በሙሉ ዶ/ር አርከበ እቁባይ ተቀብሎ የመሬት ኮሪፖሬሽን ኃላፊ ለሆነው ለአቶ አማሬ ….. አስረክበዋል፡፡ አቶ አማረ ደግሞ የአዲስ አበባን መሬት በተለያዩ ዜዴዎች የኦሮሞን አርሶ አደር በማፈናቀል ለወያኔ ያስተላለፈና በእነሱ ዘንድ ጀግና ተብሎ የሚወሰድ የመሬት ወረራ መሀንዲስ ነው፡፡ ስለዚህ የሀዋሳ መሬትም ወደ አቶ አማሬ እጅ እንዲገባ የተደረገው የወያኔን ጥቅም ማስከበር የሚችል ሰው ስለሆነ ነው፡፡
ከዚህ በፊት በሐዋሳ ከተማ የተቋቋሙ የጨርቃጨርቅ፣ የቺፑድ፣ የፔፕሲ ለስላሳ፣ የቢጂአይ ቢራ፣ እና ሌሎች ጥቃቂን ፋበሪካዎች ይገኛሉ፡፡ በእነዚህ ፋብርካዎች የሲዳማ ተወላጅ ከሆኑ ሥራ አጥ ወጣቶች መካከል ስንቱ ተቀጠሩ ከተባለ መልሱ ምንም ይሆናል፡፡ ጥቂት የተቀጠሩ ቢኖሩ እንኳ ከጉልበት ሠራተኝነት ያለፈ ሥራ አልተሰጣቸው፡፡ ስለዚህ በፋብሪካዎቹ መምጣት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስላመዘነ ፋብርካዎቹ ከሚለቁት ኬሚካሎች የተነሳ የአርሶ አደሩ ከብቶቹ ከማለቃቸውም በላይ የከተማው ህልውና የሆነው ሐይቅ እየተበከ መሆኑን የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በጥናት አረጋግጠዋል፡፡
ይህንን እውነታ እያወቅን አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ የኢንዱስትሪ ዞኑን አመጣጥ በገባዉ ልክ ሲናገር ለሲዳማ ወጣቶች ሥራ አጥነትን ለማስወገድ እንደሚጠቅምና አቶ መለስ ዜናዊ ከአማራዎች ጎሮሮ ነጥቆ ወደ ሲዳማ እንዳመጣ ለማሳመን ቢሞክርም ዋናው የወያኔ/ሕወሀት ግብ ግን ከኢንዱስትሪዉ ጋር ተያይዞ የሚገነቡትን ከ30,000 (ሰላሳ ሺ) በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለራሱ አባላት በማከፋፈል በሐዋሳ ላይ የበላይነት መያዝ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ይህንን ዓላማ ለማስፈፀምም በሲዳማ መሬት ላይ በተቋቋመው የኢንዱስትሪ ፓርክ ላይ የወላይታ ተወላጅ የተሾመ ሲሆን ይህም ለሲዳማ ልጆች ታሰቧል የተባለው የሥራ አጥነት ቅነሳም የህልም እንጀራ መሆኑን የሚያመለከት ነው፡፡
የሲዳማ ህዝብ ከኢንዱስትሪ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ከተፈለገ ከሐይቋ የተነሳ በቂ የቱሪዝም ገቢ ባላት ሐዋሳ ላይ በኢንዱስትሪ ስም የቻይና ቆሻሻ መጣያ ቤቶች ከሚገነባ ለምን የብክለት ሁኔታቸውን መቆጣጠር የሚችሉ ኢንዱስትሪዎች በይርጋዓለም ወይም በአለታ ወንዶ ከተማዎች አይቋቋምም? ስለዚህ በሀሳው እየተገነባ ያለው የኢንዱስትሪ ፓርክ ሲዳማን ለማልማትና ለመጥቀም ሳይሆን በግድለሽነት የሲዳማ ህዝብና የሐዋሳ ውበት የሆነውን ሀይቅ ለመበከልና ወያኔን በብዛት በማስፈር አካባቢውን ለመቆጣጠር እየደረገ ያለ ሴራ ስለሆነ በጥብቅ የሚወገዝ ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ለኢንዱስትሪ ፓርኩ የተወሰደዉ መሬት በሲዳማ ልማት ኮሪፖሬሽን ባለቤትነት ስር የነበረ ሲሆን በዚህ መሬት አጠገብ የአቶ ታደሴ በላይና ሌሎች እርሻዎች ሳይነኩ ለሲዳማ ሕዝብ ካላቸዉ ንቀት የተነሳ የሕዝቡን መሬት ዘርፈዋል፡፡ ይህ መሬት እንዲመለስ የሲዳማ አባቶች ጥያቄ በማቅረባቸዉ የኦሮሚያዉ ዓይነት ግርግር እንዳይፈጠር በመፍራት በሀዋሳ ዙሪያ ካለዉ መሬት ላይ የተወሰነ ሄክታር ለሲዳማ ልማት ኮሪፖሬሽን እዲሰጥ ውሳኔ ለመስጠት የሀዋሳ ከተማ የከንቲባ ኮሚቴ በተሰበሰበበት ወቅት የወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ የሆነው አቶ ታሪኩ ኡጋሞ ሀዋሳ የፌዴራል ስለሆነ ለሲዳማ ልማት የሚሰጥ መሬት የለም ...ብሎ መናገሩን ከታማኝ ምንጮች የተገኘ መረጃ ያሳያ (አቶ ታሪኩ የሀዋሳ ከነማ የስፖርት ከለብ ስፖርተኞችን በገዛበት ወቅት ከሌሎች ጋር በመሆን እስከ 11,000,000 ብር ያጭበረበረ ሲሆን የድንፋታዉም መነሻ ይህንን ወንጀሉን የሲዳማን መብት በመርገጥ ለመሸሸግ አስቦ ነው)፡፡ ግን አቶ ታሪኩ የሲዳማ ህዝብ 10 ወይ 20 ብቻ በተሰበሰበበት ይሄንን ቃል ይደግመዉ ይሁን?
የ30 አመት የሀዋሳ ማስተር ፕላንና፣ የፌዴራል ከተማ የማድረግ እቅድና ዳግም የሲዳማ ህዝብ እጣ ፋንታ
በ2008 ዓ.ም ወያኔ/ደኢህዴን የሀዋሳ ከተማን በዙሪያው ያሉ ገጠራማ ቀበሌዎችንና ትናንሽ የከተማ መንደሮችን ለመያዝ አዲስ ዕቅድ አዘጋጅቷል ይሄም ከጥቅት ወራት በኋላ የከተማዋን ተጠርነት ለፌዴራል ለማድረግ አሁን የተቋቋመዉን ሽባ መዋቅር ሲዳማዎች ማስተዳደር አልቻሉም ተብሎ በዝረራ በማባረር የተሰባጠረ መዋቅር ለመፍጠርና የከተማዋን ተጠርነት የፌዴራል ለማድረግ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ ይህ እቅድም የወጠዉና የፀደቀዉ ከኦሮሚያዉ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋ ሲሆን ሀዋሳ ላይ ግን ያለ ምንም ዉሳኔ ያለ ኮሽታ (Silent moode) እቅዱ እየተተገበረ ይገኛል ፡፡
ዕቅዱ የ30 ዓመታት የሀዋሳ ከተማ ዕድገትን (ለሲዳማ ህዝብ ጥፋትን) የያዘ ማስተር ፕላን ሲሆን በዕቅዱ ላይም የሲዳማ አመራሮች ፈርመውበታል፡፡ በሲዳማ ዞን በኩል ዕቅዱን የፈረመው የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አክልሉ አዱላ (ያለ ጊዜ የተወለደ ካቢኔ) ሲሆን ከሐወሳ ከተማ በኩል ደግሞ የማዘጋጃ ቤቱ ኃላፊ የሆነችው ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ (በእናት አማራ የሆነችው) ናት፡፡ ማስተር ፕላኑም በስተምስራቅና በስተምዕራብ የሀዋሳ ከተማ እስከ ሻማና ቃዲዳ፣ በስተደቡብ ደግሞ እስከ ሞሮቾ እንዲስፋፋና የቦርቻ ወረዳን ለሁለት ከፍሎ እስከ ዳራራ እንዲደርስ ተደርጎ የተሰራ ሲሆን አሁን በሐዋሳ ከተማ ውስጥ በክ/ከተማነት የታቀፉ 12ቱን ቀበሌዎች (በአሁኑ ጊዜ አራቱ ቀበሌዎች ማለትም ዳቶና ጫፋ ኮትጃዌሳ ሙሉ በሙሉ እንዲሁም አላሙራና ቱሎ በከፊል በሌሎች ሰፋሪዎች ተወረዋል) እንዲሁም የወንዶ ገነት ወረዳን ሙሉ በሙሉ በመዋጥ በአካባቢዉ በዕቅዱ መጨረሻ የሚኖረውን ወደ አንድ ሚሊዮን የሚደርሰውን የሲዳማ ህዝብ አፈናቅሎ በሌሎች የሚተካ ይሆናል፡፡ በዚህ ሂደትም የሃዌላ ጎሳ እንደ ኦሮሞዎቹ አብቹና ገላን ጎሳዎች ሙሉ በሙሉ የሚጠፋ ሲሆን ያናሴ፣ ማልጋ፣ ቄዌና፣ ጉጄ፣ ፋርዳኖ፣ ሀዲቾ፣...ወዘተ ጎሳዎች ደግሞ በከፍል የመጥፋትና በከፍተኛ ደረጃ የማንነት መጥፋት ስጋት ውስጥ የሚገቡ ይሆናል፡፡ የሲዳማ ልጆች ሂደቱን ካሁኑ ካልገታን በስተቀር በዚያን ጊዜ ተነስተን ብንጮህና የደም እንባ ብናለቅስ ዋጋ አይኖረውም፡፡ ወያኔ ይህንን ዕቅድ በአቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ በኩል ለማሳካት ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ እየተሯሯጠ ነው (በነገራችን ላይ አቶ ሽፈዉ ሽጉጤ በዱሜ ታቦር አካባቢ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ፕላን እንዳይሰጣቸዉ በማድረግ መሬቱ ለልማት ይፈለጋልና እናንተ ሌላ መሬት እስኪዘጋጅላችሁ ጠብቁ ብሏቸው ከዉስጥ አዋቅ ምንጮች ለማወቅ እንደተቻለዉ መሬቱን ለዉዱ ጓደኛዉ ለአቶ ዱካሌ ዋቃዮ ሪዞርት መስርያነት ተብሎ እየተሰራ ያለ ድራማ እንደ ሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ምን ዓይነት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የሚሰራ ጨካኝና ርህራሄ የሌለዉ ሰው ነዉ?)፡፡

የመጨረሻ መልዕክት
በዚህ ሀገር ውስጥ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የእኩልነትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች በተግባር እስካልተተረጎመ ድረስ ህዝቡ እጁን አጣጥፎ በዝምታ ሊመለከት አይገባም፡፡ ኢኮኖሚውንና ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችን ወያኔና አጋሮቹ ተቆጣጥረው ባሉበት፣ የመሬት ባለቤት የሆነውን ህዝብ እያፈናቀሉ በመውረር በቦታው ሌላ ማንነት የመተካት ስትራቴጂ ተነድፎ በሚፈጸምበት፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ከፍትህ ጋር ተቀብረው ዜጎች በጠመንጃ ኃይል ታፍነው በሚኖሩበት፣ ከሰለሞን መስመር (Solomonic Lineage) በስተቀር ሌሎች ህዝቦች ኢትዮጵያን መምራት እንደማይችሉና ለኢትዮጵያ ጥቅም እኩል ኃላፊነት እንደማይሰማቸው በሚታመንበት ሀገር ውስጥ እንዴት በጋራ መኖር ይቻላል? ይህንን ሁኔታ ለማስቀየር የደምና የአጥንት ዋጋ ብጠይቀንም እንኳ ኃይላችንን አሰባስበን ከመታገል ውጪ በዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ መንገድ አሁን ያለውን ጭቆና የማስወገድ ዕድል ዝግ ነው፡፡
እናንተ ወያኔዎች! የምንሰጣችሁ ምክረ-ሀሳብ ባይኖርም ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በመጽሀፋቸዉ ውስጥ እንዳሉት በታሪክ አጋጣሚ ስልጣን በእናንተ እጅ ወድቋል፡፡ ይህንን ስልጣን ያለአግባብ ተጠቅማችሁ በበረሀ እያላችሁ ስትምሉ የነበራችሁትን የህዝብን ሰብአዊ፣ ዲክራስያዊና ኢኮኖሚያዊ መብት ማክበርና ማሰከበር ትታችሁ ከደርግ በባሰ ሁኔታ የህዝቡን መብት ገፋችኋል፡፡ ይህንን ጭቆና ስትፈጽሙ ስንመለከት የትግላችሁ ዓላማ የነበረው የህዝባችንን ሀብት መዝረፍና ለራሳችሁ የምትፈጥሩትን የትግራይ ሪፐብሊክ ማጠናከር እንደሆነ ከመገንዘባችንም በላይ የደርግ መንግስት ተቃውሞ የሚያሰማውንና መብቱን ለማስከበር የሚንቀሳቀሰውን ህዝብ በአሸባሪነት እየደፈረጀ እንደገደለው ሁሉ ይህንኑን ታሪክ እናንተ በመድገማችሁ ምንም ዓይነት ስብዕና የሌላችሁ ባንዳዎች መሆናችሁን ለመረዳት ችለናል፡፡
አሁንም እናንተ ወያኔዎች! በከተማ መስፋፋት ስትራቴጂያችሁ የኦሮሚያን፣ የሲዳማንና የሌሎች ጭቁን ህዝቦችን መሬት እየወረራችሁና እየሸጣችሁ በህዝብ ማንነትና ጥቅም ላይ ጦርነት ከፍታችኋል፡፡ በተለይም በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየፈፀማችሁ ያላችሁት የዘር ማጥፋትና የአፈና ተግባር በዝምታ የምንመለከተው አይሆንም፡፡ በሲዳማ ህዝብ ላይም በሰጣችሁት ኢፍትሐዊ ፍርድ ህዝቡ ማንነቱ የሆነውን ቋንቋዉንና ባህሉን ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ እንዳይችልና የብሄሩ ስም “ደቡብ” ተብሎ እንዲጠራ አድርጋችኋል፤ ባለፉት ስርዓቶች የደረሰብንን በደል የምንረሳዉ ባይሆንም በአሁኑ ሰአት ለእኛ ነፍጠኛ ሆናችሁ ቁጥራችን በእናንተ አቆጣጠር እንኳ 5,500,000 (አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ) በላይ ሆኖ እያለ እውነታዉን በመሸፈን ራሳችንን በራሳችን እንዳናስተዳድር በይስሙላ ዲሞክራስ (Pseudo-democracy) እየገዛችሁን ያላችሁት ቀንደኛ ጠላታቶቻችን እናንተ ወያኔዎችና ተላላክያችሁ ደኢህዴን መሆኑን ህዝባችን ተገንዝቧል፡፡ ከዚህም ባለፈ ትግሉ መራራ የደምና የአጥንት ዋጋ ቢያስከፍለንም እንኳን ቀደምት አባቶቻችን እንዳደረጉረት ሁሉ ታግለን ከጭቆናችሁ ነፃ ለመውጣት ወንድማችን ከሆነውና ከጭቁኑ የኦሮሞና የሌሎች ህዝብ የትግል አጋሮች ጋር አንድ ሆነን እንፋለማችኋለን፤ በዚህም ማንንም ሳናስፈቅድ እኛ የሲዳማ ብሔር የራሳችንን ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በቅርቡ እንደምንመሰርት ልታዉቁ ይገባል፡፡ በዚህ ሂደት ማሰር፣ መግደል፣ ማሳደድ... ስራችሁ እንደሆነ ህዝቡ በውል መረዳቱንና ይህንን ፈርቶ ትግሉን እንዳማያቆም ጠንቅቃችሁ ሊታውቁ ይገባል፡፡ ስለዚህ የሲዳማ ህዝብም ልክ የኦሮሞ ጀግኖች ለነፃነት እያካሄዱ ያሉትን ሞዴል በመከተል አሁን የጀመረውን የትግል መስመር አጠናክሮ በመቀጠል ነፃ እንደሚወጣ፣ ከህዝብ ተነጥሎ ብቻውን የቀረው የእናንተ መዋቅር እንደ እንቧይ ካብ በአንድ ምሽት ፈርሶ የሚያድር መሆኑን እንዲትገነዘቡና እስካሁን ድረስ በሠራዊታችሁና በደህንነት መረባችሁ በሰራችሁት የግፍ ተግባርና የዘር ማጥፋት ወንጀል መጠየቃችሁ እንደማይቀር አበክረን እናስገነዝባችኋለን፡፡
አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ! ከዱሮ ጀምሮ የራስን ህዝብ ክዶ ባንዳ መሆን የህዝብን ትግል ማቆም እንዳማይችል ታውቃለህን? አንተ የወያኔን ተልዕኮ በመቀበል በሲዳማ ህዝብ ላይ ባደረስከው ወከባና እንግልት የራስህ ደም የሆኑ የህዝቡ ወገንተኛ ልጆች ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተሰደዋል፣ ተገድለዋል፣ ቤተሰቦቻቸው ተርበዋል፡፡ ለመሆኑ አንተ የድርጅቱን፣ የክልሉንና የፌደራል መንግስቱን ስልጣን ከያዝክ ወዲህ በሲዳማ ዉስጥ ስንቱ አርሶ አደር ከረሀብ ወጣ? ስንቱ ነጋዴ ከጉልት ስራ ወደ ኢንቨስትመንት ተሸጋገረ? ምን ያህሉ ተማሪ ዉጤታማ ሆኖ ወደ ዩኒርሲቲና ኮሌጆች ገብቶ ተወዳዳሪ ሆኖ ተመረቀ? በሀዋሳ ከተማ ውስጥ የሲዳማ ማንነት ተጠብቆ እንዲቆይና የሲዳማ ህዝብ የመሬት ባለቤትነት እንዲረጋገጥ ያከናወንካቸዉ ተግባራት ምንድን ናቸዉ? አንተ የፈጠርከዉ ሽባ መዋቅር ምን ለጥፋት ውጪ ምን ልማት ሰራ? የሲዳማን ጥቅም ቀብረህ የህዝቡን ዲሞክራሲያ ብሄርተኝነት በመደቆስህና በማሸማቀቅህ ምን ፈየደልህ? የእኛ ጀግና የሆኑት እነ ዶ/ር ወላሳ ላዊሶ ያሉ ልጆቻችን በነበራቸዉ ራዕይ የሠሩትን መልካም ታሪክ በፍፁም አንረሳውም፤ አንተ የምትንቃቸዉ እነ ብርሃኑ ሀንካራ፣ ግርማ ጩሉቄ፣ ዋቃዮ ዳማሳ የሲዳማን ብሄርተኝነት አራምደዉ የህዝቡን ክብር አስጠብቀዋል፡፡ አንተ ግን የሲዳማን ብሄርተኝነት ለመበተንና ህዝቡን ለማንበርከክ በያስከዉ ዓላማ ማፈር ሲገባህ ራዕይ የነበራቸዉን ምሁራን ትንቃለህ፡፡ ምናልባትም የሲዳማን ምሁራን በማሸማቀቅ፣ በማሰርና በማሳደድ ዘለቄታዊና ዳጎስ ያለ ስልጣን ይዥ እቀጥላለሁ ብለህ ካሰብክ ተሳስተሀል፡፡ ህዝባችን አንተ የሚታደርስበትን ማንገላታት ቀርቶ ጨካኞቹን ሥርዓቶች እየታገለ ማንነቱን በደሙና በአጥንቱ አስከብሮ የኖረ ህዝብ በመሆኑ አሁንም ይህንኑን ጀግንነት ተጠቅሞ ላንተና ለወያኔ የሚገባችሁን ዋጋ ክእጥፍ በላይ ጨምሮ እንደሚከፍላችሁ አትዘንጋ፡፡ (Gudumaaleho Rumonni Rumo Alata Wonddi Katami Hari Giddo Hiikite Tidhantanno.... Sidaamu Daga Rumo Xaano Hoodekki Hadho!!)
አንዳንድ የሲዳማ የቡና ነጋዴዎች! በዘሪሁን ቃምሶ የሚትመሩ ጥቂት የሲዳማ የቡና ነጋዴዎች በራሳችሁ የማኔጅመንት ችግር የደረሰባችሁን ኪሳራ የሲዳማን ማንነት ሽጣችሁ ከወያኔ/ደኢህዴን ማካካሻ ለማግኘት በዘርሁን ቃሚሶ መሪነት ወደ ቤቴመንግስቱ የተለያዩ የሲዳማን ማንነት የሚነኩ መረጃዎችን ይዛችሁ እየተንቀሳቀሳችሁ መሆናችሁ ይታወቃል፡፡ ዘሪሁን ቃምሶ ከመጀመሪያዉ ጀምሮ በስለላ መዋቅር ውስጥ አባል በመሆን የሲዳማን ማንነትና ትግል እየተፈታተነ ያለ ሞላጫ ሌባ መሆኑን እያወቃችሁ ለምን ከዚህ አውሬ ጋር ትተባበራላች? ስለዚህ ምንም እንኳን የደረሰባችሁ ኪሳራ አስከፊና የቢዝነሳችሁን ቀጣይነት የሚፈታተን ቢሆንም ይህንን ለማካካስ ግን የህዝብን ማንነት መሸጥ ስለማይቻል ዞር ብላችሁ እራሳችሁን ብትመለከቱ መልካም ነው፡፡
የሲዳማ ምሁራን! ወያኔ ከሚከተላቸዉ ስልቶች አንዱ በህዝቡ ዉስጥ የሚፈጠሩትን አነቃቂ ታጋዮች (Activists) ማጥፋትና በጎሳ ከፋፍሎ እርስ በርስ በማፋጀት ዕድሜውን ማራዘም ነው፡፡ የሲዳማ ምሁራን በተለያዩ ጊዜያት ለእስር፣ ለስደትና ለእንግልት የተዳረጋችሁ ቢሆንም ለዚህ ዓይነቱ ግፍ እጃችሁን ሳትሰጡ ከተሸማቀቃችሁበት አጥር ክልል ወጥታችሁ ህዝብን ነፃ ቢያወጣ ትግል ሂደት ውስጥ ተሳታፊ ሊትሆኑ ይገባል፡፡ ለዚህም በቅርብ በኦሮሚያ ውስጥ ወያኔ የሚያካሂደውን የዘር ማጥፋትና የመሬት ወረራ ከተቃወሙ አነቃቂ ታጋዮችና ደጋፊዎች መካከል ከ38000 (ሰላሳ ስምንት ሺ) የሚበልጡት የታሱሩና ከ1000 (አንድ ሺ) የሚበልጡት የተገደሉ ቢሆንም ብሶት የወለደው ትግል በመሆኑ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉ ለእኛ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ በመሆኑም የሲዳማ ምሁራን ካንቀላፋንበት በመንቃት የህዝቡን ትግል ስልታዊ በሆነ መንገድ በዕውቃታችን ከመምራት ባለፈ አነቃቂ ታጋዮች (Activists) በትግል ሂደት በአምባገነኑ የወያኔ/ደኢህዴን ቡድን ለእስር በሚዳረጉበት ወቅት ለእነሱና ለቤቴሰቦቻቸው አስፈላጊውን በምስጢር ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ከዚህ ዉጪ በዝምታ ቁጭ ብለን ብንማረር የምንመኘዉን ነጻነት ማግኘተ እንደማንችል በምሁራዊ አዕምሯችን መተንተን ያስፈልጋል፡፡ የትግል ስልቱን በተመለከተም አንደኛው አማራጭ የሲዳማን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን ) ተቀላቅሎ ማጠናከር ሲሆን ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ ሌላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መፍጠር የሚችል በዕውቀትና በሀብት ጠንካራ ድርጅት በማቋቋም መታገልና የሲዳማን የነፃነት ትግል ፈር ማስያዝ ነው፡፡ ዝምታ ወርቅ ሳይሆን የጭቆና ጊዜ የሚያራዝም ነቀርሳ መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡
ቀጣዩ የትግል አካሄዳችን ቁልፍ ኃይላችን የሆነውን ህዝባችንን የትግሉ ባለቤት በማድረግ በዚህ ጽሁፍ ተዘርዝረዉ የቀረቡትን ችግሮችና አደጋዎች ነጻ ለማዉጣት በአንድ በኩል ከነባሩ አካሄድ ወጣ ያለ የአደረጃጀት ስልት በሌላ በኩል ደግሞ የእይታ ለዉጥ ማምጣት ይጠበቅብናል፡፡ በዚህ ሂደት ሳንሰለችና ሳንታክት ለህዝባችን የትግል ጥሪዎች እያስተላለፍን ንቅናቄ ማካሄድ አለብን፡፡ የእይታ ለዉጡም የዘመናት ጥያቄ የሆነዉን የሲዳማን ብሄር የራስን በራስ የማስተዳደር መብቱ ማረጋገጥ የምንችለዉ በወያኔ/ኢህአዴግ መስመር ሣይሆን ይህ ስርዓት ሲለወጥ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ ስልታዊና ስትራቴጅያዊ አጋርነት (Strategic and Tactical Alliance) ከተለያዩ ተራማጅ ድርጅቶች ጋር መፍጠር እንደሚገባ አምኖና ተቀብሎ መታገል ነው፡፡ ለዚህም "አንድ ዱጉና ዱባላ" ብቻ ሳይሆን "ብዙ ዱጉና ዱባላዎች" ሆነን መዉጣትና የህዝቡን ትግል መምራት ይገባናል፡፡ ትግሉ መራራ ቢሆንም እየመጣ ካለዉና ከሚመጣዉ አደጋ ጋር ሲመዛዘን ግን መስዋዕትነቱ ዕምንትና ማንነትን ከማጣት እንደማይበልጥ መገንዘብ ይገባል፡፡ የአሜርካኑ የቢዚነስ ጸሀፍ የሆነዉ ምሁር (Don't Pave On A Cow Pathe) ይላል አባባሉም በተለመደዉ መንገድ ብቻ አትጓዝ እንደማለት ሲሆን፡ ከአባባሉ ተነስተን እኛም የሲዳማን ህዝብ ነፃ ለማዉጣት የመጣንበትን መንገድ ከፖለቲካ ቢዚነስ ህግ አንፃር በመፈተሸ አዋጭ መንገድ መምረጥ ይገባናል፡፡
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አመራሮችና አባላት! ፖለቲካ በየዋህነትና በደፈና የሚመራ ሳይንስ አይደለም፤ ድል ለመቀዳጀትና የህዝብን ነፃነት ለማረጋገጥ መስዋዕትነት መክፈልና ሂደቱን በዕውቀትና በጠንካራ አንድነት መምራት ግድ ይላል፡፡ ሲአን እንደ ድርጅት ተቋቁሞ በወጣ ገባ ትግል ሂደት ባሳለፈባቸው ያለፉት 35 ዓመታት ህዝባችን ዋጋ የሚሰጠውን መስዋዕትነት እየከፈለ የመጣ ድርጅት ቢሆንም አሁን ባለው ቁመና ግን የህዝባችንን ጥያቄ ለመመለስ በሚያስችለው መስመር ላይ ነው ብሎ ለመውሰድ ያዳግታል፡፡ ስለዚህ ድርጅቱ ራሱን በመገምገምና የሲዳማን ህዝብ ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል ፖለቲካ ማራመድ ወቅቱ የሚጠይቀዉ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ስትራቴጂያዊና ስልታዊ አካሄድን፣ የመሪነት ሚናን፣ የደህንነት መረጃ ቅብብሎሽና አያያዝን በመፈተሸ መጓዝ ይገባል፡፡ ለምሳሌ የድርጅቱ መረጃ ለአቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ የሚደርሰዉ በአቶ አሰፋ ዱካሞ በኩል ሲሆን ለአሰፋ ዱካሞ መረጃውን የሚያቀብለው የእናንተ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆነ ግለሰብ ሲሆን ይህንን የሚያደርገው በየዋህነት ወይስ ደርጅቱን ለመጉዳት ሆን ብሎ እንደሆነ ማወቅ አልተቻለም፡፡ ስለዚህ ለአንድ ጠንካራ ድርጅት የመረጃ ምስጢራዊነት ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ የደርጅቱን የደህንነት መረብ በጠንካራ ኃይል በማዋቀር የሲዳማን ህዝብ ቁመና የሚመጥንና በህዝቡ ውስጥ ንቅናቄ ለመፍጠር የሚያስችሉ የትግል ስልቶችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ ለነፃነት መትጋት ያስፈልጋል በሌላ መልኩ ህዝቡ ዉስጥ ያለዉን ችግር ነቅሶ በማዉጣትና ለዝያ ችግር የሚሆን የፖለቲካ ትንታኔ በማቅረብና የተለያዩ ወቅታዊ ሰነዶችን እያዘጋጁ አባላቱንና ህዝቡን ማነቃቃት የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ተግባር ቢሆንም አንድት ገጽ መግለጫ እየፃፉ ህዚቡን ነፃ ማዉጣት አይቻልምና፡፡
በህደቱ የፋይናንስ ችግር እናዳለባችሁ ይገባናል ይሁንና የፋይናንስ አሰባሰባችሁም ምስጥራዊ ካልሆነና እጌሌ 10,000 ሰጥቶናልና አንተ ስንት ትሰጠናለህ አይነት ከሆነ ዉጤቱም የብሄሩን ደጋፍ አባላት ለወያኔ ጩሉለዎች አሳልፎ መስጠት ይሆናልና ስለዚህ እንደ ድርጅት ራሳችሁን መገምገም ያለባችሁ በአመቱ ዉስጥ ስንት መድረኮች ተዘጋጅተዉ አባላት፣ ህዝቡ፣ ከህዝቡም መካከል ተተኪ ሀይሉ በተለይ ወጣቱ ተነቃቃ? ይሄ ካልሆነ ከስም ያለፈ የፖለቲካ ስራ ሰርተናል ብለን እናምናለን ወይ? እየታገንለት ያለዉ አላማ፣ ፕሮግራምና ግብ ከአጭርና ከረዥም ጊዜ አንፃር ምንድ ነዉ? አላማችንና እቅዳችን ወደ አባሉና ህዝቡ ደርሰዋል ወይ? ህዝቡን ከጨቋኞች ለመከላከል የፈጠርነዉ ህዝባዊ ስልት ምንድ ነዉ? የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ለእናንተዉ ተዋለሁ፡፡ በመጨረሻም ለእነዚህ ጥያቄዎች የመጣንበትን መንገድ ገምግመን ትክክለኛ መልስ ካልመለስን ድርጅቱ በምርጫ ሰሞን ከመንቀሳቀስና መግለጫ ከማዉጣት አልፎ የህዝቡን ጥቅም ያስከብራል ብሎ ተስፋ ማድረግ ከባድ ይሆናል ምክንያቱም ትናንት በነበረን የአስተሳሰብ ደረጃና ቁመና ዛሬንና ነገን መምራት አዳጋች ነዉና፡፡
የሲዳማ ህዝብ! ከምንሊክ ጀምሮ የተጫነብህን የጭቆና ቀንበር ከላይህ ለማሽቀንጠር ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለሀል፡፡ ይሁንና አሁን በስልጣን ላይ ባለው የወያኔ ቡድን የጭቆና መረቡ ወደለየለት ደረጃ በመሸጋገሩ ትግልህ ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክረህ መቀጠል አለብህ፡፡ የወያኔ ቡድን በማንነትህ ላይ ባካሄደው ጭቆና ባህልህ ጠፍቷል፣ በከተማ አካባቢ ማንነትህ ሞቷል፡፡ ለአብነትም የሉዋ ሥርዓትህ የደበዘዘ ሲሆን፣ ቋንቋህ የስራ ቋንቋ ነዉ የተባለዉም ለይስሙላ ነዉ፡፡ ባህልህንና ቋንቋህን /ሲዳሙ አፎ/ እስከ ክልል ድረስ ማሳደግና መጠቀም እንዳትችል ከሌሎች መልከ-ብዙ ብሔሮች ጋር እንደጨርቅ ተሰፍተህ እንዲትኖር ተገደሀል፣ ሌላው ቀርቶ በሀዋሳ ከተማ በመንግስት መስሪያ ቤቶችና በትምህርት ቤቶች በስራ ላይ እንዲውል ተደረገውን ቋንቋህን እነ አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ ሴራ በቀመሩት ሴራ በአማርኛ ቋንቋ ተተክቷል፡፡ በ1994 ዓ.ም የወጣው የሀዋሳ ከተማን በስብጥር ማስተዳደር የሚለው ደንብ ባለመለወጡ በከተማ አስተዳሩና በሰባቱ ክፍለ ከተሞች በፖሊስ አዛዥነት፣ በገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊነት፣ በክፍለ ከተማ አስተዳዳሪነት፣ በድርጅት ሀላፊነት፤ በክፍለ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅነት፤ በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊነት፣ በአጠቃላይ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የስልጣን ወንበሮች መካከል 50% መጤ ብሄረሰቦች እንዲሾሙ የተደረገ ሲሆን የአንተ ልጆች በሌላ ከተማ ሄደው ሳይሾሙ በራስህ ከተማ ላይ ሌሎች ሥልጣን እንዲይዙ የተደረገው መሬቱንና የቀበሌ ቤቶችን ለወያኔና ኢህዘደግ ለሚፈልገው ወገን በቀላሉ ለማስተላለፍ ተብሎ ነው ፡፡ ይህ ድርጊት በኢትዮጵያ ዉስጥ በየትኛውም የብሔር ከተማ ያልተከናወነ ሲሆን ወያኔ/ኢህአዴግ ዳግም ምኒሊክ በመሆን በመሬትህ ላይ ራስህን በራስህ እንዳታስተዳድር በማድረግ ሀብትህን እየዘረፈ ነዉ፡፡ በ1994 ዓ.ም የሀዋሳ ከተማን በስብጥራ ማስተዳደርን አስመልክቶ የወጣውን ደንብ በመቃወም ግንቦት 16 በወጡ የሲዳማ ህፃናት፣ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ላይ የከባድ መሳሪያ ጭፍጨፋ ተካሂዶ በርካታዎቹ የተሰዉ ሲሆን የእነዚህ ሰማዕታት ደም ባዶ እንዳይቀርና በሐዋሳ ላይ የምኖርህን ጥቅም ለማስከበር በተለመደው ወኔህ ጨቋኞችህን በቃ ልትል ይገባል፡፡
የሲዳማ ወጣቶች! አሁን ላለንበት የአካባቢያችን ቀዉስና የህዝባችን ጭቆና ዋነኛ ነቀርሳ የወያኔ ስርዓት ነዉ፡፡ የወያኔ አካሄድ የህዝባችንን ማንነት አጥፍቶና ሀብታችንን ዘርፎ በሂደት የራሱን ነፃ ሪፐብሊክ (ሀገር) መፍጠር መሆኑን ልብ ብላችሁ ልትገነዘቡ ይገባል፡፡ ወጣጦቻችን በሥራ አጥነትና በድህነት ውስጥ ተዘፍቀው የቆዩት ወያኔ በሰራው የግፍ ተግባር ነው፡፡ ይህ የወያኔ አካሄድ በዚህ ከቀጠለ ህዝባችን ለከፋ ድህነት፣ ሥራ አጥነት፣ ስደት፣ ጦርነትና እልቅት እንደሚጋለጥ እሙን ነው፡፡ ስለዚህ ለእዉነተኛ ኢከኖሚያዊና የማንነት እኩልነት፣ ለፍትህ፣ ለሰብዓዊና ለዲሞክርሲያዊ መብቶች መከበርና ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ተጠቅመን የሲዳማን ክልላዊ መንግስት ለማቋቋም በቁርጠኝነት በመነሳት መታገልና ጭቆናውን በቃ ማለት ይገባል፡፡ ይህም ከቃል አልፎ ወደ ተግባር መለወጥ አለበት፡፡ ጭቆና በትግልና በመስዋዕትነት እንጂ በቃ ስለተባለ ብቻ አይበቃም፡፡ በዚህ ዘመን እንደ እያርኮ በጩኸት የሚፈርስ ግንብ የለም፡፡ እናንተ ጀግና የሲዳማ ወጣጦች ወንድማችሁ ሆነው የኦሮሞ ወጣቶች ጎን በመሰለፍ ትግሉን መቀላቀልና የበኩላችሁን ሚና መጫወት የጊዜዉ ወሳኝ አጀንዳ ነው፡፡ ይህም ማለት በኦሮሞ ህዝብ ጎን በመሰለፍ መታገል ብቻ ሳይሆን ተሞክሮውን ወደ ሀዋሳ ከተማ በማምጣት በእድገት ስም እየጠፋ ያለውን ማንነትህን ከጥፋት መታደግና እየተዘረፈ ያለውን መሬትህን ከወረራ መከላከል አለብህ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ጠንካራ አንድነትና አደረጃጀት ፈጥራችሁና ፍርሀት አስወግዳችሁ ወቅቱ የሚጠይቀዉን መስዋዕትነት መክፈል ይገባችኋል (እዚህ ላይ በአንድ ወቅት እስራኤልን በፕሬዝዳንትነት ይመራ የነበረዉ ይስሀቅ ራቢን የኢየሩሳሌም ከተማ አካል የሆነዉን ዌስት ባንክን ለፍልስጤሞች ለመስጠት ድርድሩን ጨርሶ ለህዝቡ ይፋ ሲያደርግ አንድ የአይሁድ ጀግና ወጣት ነዉ በፕሩዝደንቱ ላይ እርምጃ በመዉሰድ እቅዱን ያከሸፈዉና ያስቆመዉ፡፡ የወጣቱ እርምጃ የእናት አገሩን መሬት ማዳን ከመቻሉም በላይ በዉጤቱም እነ ሻሮንና ቤኒያምን ዓይነት ጀግና መሪዎች ማፍራት አስችሏል፡፡ ስለዚህ እኛም የሲዳማ ወጣቶች ከዚህ ወጣት ምን መማር ይገባናል?)
ከዚህ መነሻነትም በዶ/ር ወላሳ ላዊሶ የተጀመረውን የልማት ራዕይ ማለትም የጋራንባ ኮንስትራክሽን፣ የሲዳማ የቴክኖሎጂ ጋራዥ(እንደ መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅኔሪንግ ኮርፖሬሽን ይሆን የነበረ)፣ የሲዳማ ማይክሮ ፋይናንስ (ወደ ባንክ የሚያድግ የነበረ)፣ ፉራ ኮሌጅ(ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያድግ የነበረ)..... እና ሌሎች ሲዳማን ከወቅቱ አለም አቀፍ ሁኔታ ጋር ወደፊት እንድሄድ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች በእነ አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ በመኮላሸታቸው ለህዝባችን ሳይጠቅሙ መቅረታቸውን ለህዝቡ በማሳወቅና ግንዛቤ በመፍጠር መንቀሳቀስ ይገባል፡፡ ያ ራዕይ ቢሳካ ዛሬ በሐዋሳ ከተማ ለወያኔዎች በሚገነባዉ ኢንዱስትሪ ዞን ላይ የሲዳማ ህዝብ የተለያዩ አካባቢን የማይበክሉ ኢንዲስትሪዎች በመገንባት ልማቱን ያሳልጥ ነበር፡፡
በአጠቃላይ እኛ የሲዳማ ወጣቶች በተለይ በመጤ የደኢህዴን አሽከር አመራሮች ላይ የተክሉ ዮታን ሞዴል በመከተል የሀዋሳ ከተማ ምቹ እንዳይሆንላቸዉ ለማድረግ የጋራና የተናጠል እርምጃ መዉሰድና የጭቆና መረባቸውን መበጣጠስ ይገባናል፡፡ ኢኮኖሚስቱ Adam Smith “There is no free lunch” እንዳለው በነፃ የሚገኝ መብት የለምና መስዋዕትነት እንክፈል፡፡ ይህ ካልሆነ ዛሬ የምንወደውን ቋንቋችን፣ ባህላችን፣ ዕሴቶቻችን፣ መሬታችንና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብታችን ከፍተኛ አደጋ ዉስጥ መሆኑን በውል ልንገነዘብ ይገባል፡፡
በተመሳሳይ ርዕስ ሌሎች ጽፎችን ይዘን እስክንገናኝ ድረስ መልካም የትግል ጊዜ ይሁንልን፡፡
ድልና ድምቀት ለሰፊው የሲዳማ ህዝብ!!!

Source:https://www.facebook.com/tadesse.washo