Gudumaale

   Sidaamu Daga Budu Battala
Connecting Sidama People

በአቶ ሐይሌማርያም የምመራዉ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዋሳ ከተማ እጣ ፈንታን በተመለከተ ያደሬገዉ ዝግ ስብሳባና ዉሳኔዎቹ

ሰሞኑን ህዎሃት ከገባበት ቀዉስ ራሱን ለማዳን በመቀሌ ከተማ በዝግ ስብሰባ ተዎጥሮ ባለበት ግዜ፡ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በጠቅላይ ምንስቴር ሃይሌማርያም ደሳለኝና የፀጥታዉ ሃላፍ በአቶ ስራጅ ፋገሳ መርኔት የክልሉ ምክር ቤት 182ኛ ስብሳባ በዝግ በማድሬግ በሃዋሳ ከተማ የዎዴፍት ሁኔታዎች ላይ ዉሳኔዎችን በማሳለፍ አጽድቆል።ይህ ዉሳኔ የከተማዉ ባሌበት ከሆኔዉ ከስዳማ ሕዝብ እዉቅና ዉጭ የተፈጸመ ሌላኛዉ ዎንጀል ኔዉ። በዝሁ ስብሳባ የተካፈሌ የምክር በቱ አባል የሆኔ የስዳማ ተዎላጅ ይሳተፍ አይሳተፍ እስካሁን የታዎቀ ነገር የለም።

ከአምስት አመት በፍት ተመሳሳይ ስብሳባ ተደርጎ ተካፋይ ከነቤሩ ስዳማች በኩል ፈትልኮ በዎጣዉ ሰኔድ መሰረት የስዳማ ሕዝብ በቁጣ በመነሳቱ ሃሳቡ በእንጭጩ እንድከሽፍ ማድረጉ የምታዎስ ነዉ።

ይሁን እንጅ በስዉር ለመተግበር ማሴብ የጀመሩትግን ዎድያዉኑነበር።፡ በቀን 21/12/2006 ዓ. ም የክልሉ ርዕሰ-መስተዳደር፣አቶ ደሴ ዳልቄ በሀዌላ ቱላ ክ/ ከተማ ለአደራሽ ምረቃት ተጋብዟው ንግግር እያደረጉ ቃል ገብቶ መመለሱ ይህንን እዉኔታ ያንጼባርቃል፡ ፡ ከዚህ ቦኃላ አሉ ርዕሰ-መስተዳደሩ ቱላ ክ / ከተማ መባሏን ቀርቶ በወረዳ ሥም እድትተዳደር ቱላን እራሱ የቻለ ወረዳ እናደርጋለን ብሎ ቃል መግባታቸውን ይታዎሳል።

ከአስራ ስድስት አመት በፍትም በተሞከረዉ የሃዋሳን ከተማ ከስዳማ አገዛዝ ዎዴ ማእከላዊ መንግስት እንድሻገር ከተዎሰኔ በኋዋላ በተደረገዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ ወቅት በሃይሌማርያም ቀዳም መርነት በተካሀደዉ ጭፍጨፋ ከ69 ንጹሃን የሲዳማ ተዎላጆች ህይዎታቸዉን ማጣታቸዉ የምዘነጋ አይደለም።

በኤፍ.ቢ.ሲ የተሰራጨዉን ዘገባ ቀጥለዉ ይመልከቱ፦

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የሀዋሳ ከተማን የክፍለ ከተማና የቀበሌ አደረጃጀት እንዲሁም የቀበሌ መንግሥታዊ ተቋማት አወቃቀርን አፀደቀ።

በዚህም መሠረት የሀዋሳ ከተማ በ3 ክፍለ ከተማና እያንዳንዱ ክፍለ ከተማ በ3 ቀበሌዎች እንዲደራጅ ምርክ ቤቱ አጽድቋል።

እንዲሁም የቱላ ክፍለ ከተማ 2 የከተማ ቀበሌዎችንና 9 የገጠር ቀበሌዎችን ይዞ ቀድሞ በነበረበት አወቃቀር እንዲቆይ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብም ምክር ቤቱ ተቀብሎ አጽድቋል።

በቱላ ክፍለ ከተማ ስር የተዋቀሩት ሁለቱ የከተማ ቀበሌዎች የራሳቸው ስኬች ፕላን እንደሚኖራቸውም ተመልክቷል።

የቀበሌ አከላለልና ስያሜን በተመለከተም የአገልግሎት ተደራሽነትና ምቹነትን መሠረት ባደረገ መልኩ የክልሉ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ከከተማ አስተዳደሩና ከህዝቡ ጋር በመወያየት መስፈርቱን ሳያጓድል እንዲፈጽም ምክር ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በተያያዘ ምክር ቤቱ የክልሉ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ የደረጃ ለውጥ እንዲደረግላቸው ካቀረባቸው 13 ከተሞች መካከል መስፈርቱን ያሟሉ የ9 ከተሞችን ጥናት አጽድቋል።

በጥናቱ መሠረት መስፈርቱን አሟልተው የፈርጅ 3 ደረጃ የፀደቀላቸው ወንዶ ገነት፣ አለታ ጩኮ፣ ካራት፣ ጉኑኖ ሐሙስ፣ ጊንቢቹ፣ ገደብ፣ ገሱባ፣ ጃጁራና ጨለለቅቱ ከተሞች መሆናቸው ታውቋል።

ሌሎች መስፈርቱን ያላሟሉ ከተሞች ጥናት ተጨማሪ ጊዜ ተወስዶ እንዲታይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ሌሎች ከተሞችን እንደዚሁ የከተማ ባህሪ የሚታይባቸውንና በከተማ ሊካለሉ የሚችሉትን የመደገፍና በጥናት በመለየት የማቅረብ ስራውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ምክር ቤቱ አመልክቷል።

መረጃውን ከደቡብ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው ያገኘነው።